ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ (Balefkubet Menged Lenie Tetenqeqo)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ማዕበሉ ፡ ሳይጥለኝ ፡ ውሃውም ፡ ሳያሰጥመኝ
እጄን ፡ በእጁ ፡ ይዞ ፡ ወንዙን ፡ አሻገረኝ
የፈተናው ፡ እሳት ፡ ወላፈን ፡ ሳይጎዳኝ
በጌታዬ ፡ ፀጋ ፡ በሕይወት ፡ አለፍኩት

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ ያደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
ሃገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ

ከሕያዋን ፡ ጋር ፡ ኖሬ ፡ እንዳከብርህ
ፈተናን ፡ አልፌ ፡ እንዳመሰግንህ
ኢየሱስ ፡ ከጐኔ ፡ ቆሞ ፡ አበረታኝ
ከአንበሳው ፡ አፍም ፡ ደጋግሞ ፡ አወጣኝ

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ አደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
አገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ

ሕይወቴን ፡ ለአምላኬ ፡ አደራ ፡ እየሰጠሁ
በእረኝነቱ ፡ ስር ፡ ሳልሰጋ ፡ እኖራለሁ
ከክንፎቹ ፡ በታች ፡ እተማመናለሁ
በእርሱ ፡ ተጠብቄ ፡ ሃገሬ ፡ እገባለሁ

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ አደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
አገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ

ጌታ ፡ የሰራውን ፡ ድንቅ ፡ አስታውሳለሁ
ስላፈው ፡ ዘመን ፡ አመሰግናለሁ
ከፊቴ ፡ ላለውም ፡ በእርሱ ፡ እደገፋለሁ
በዘለዓለም ፡ ክንዱ ፡ በእቅፉ ፡ እኖራለሁ

አዝ፦ ባለፍኩበት ፡ መንገድ ፡ ለእኔ ፡ ተጠንቅቆ
እዚህ ፡ አደረሰኝ ፡ ከክፉ ፡ ጠብቆ
እስከ ፡ ፍጻሜውም ፡ ያቆመኛል ፡ ጌታ
አገሬ ፡ እገባለሁ ፡ እምነቴ ፡ ሳይፈታ