ዐይኖቼን ፡ ከመስቀልህ ፡ አንስቼ (Aynochien Kemesqeleh Ansechie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ዐይኖቼን ፡ ከመስቀልህ ፡ አንስቼ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ (፪x)

የሕይወቴ ፡ ሰላም ፡ ሁሉ ፡ የሚፈልቅበት
ከጭንቀትም ፡ ሁሉ ፡ ልቤ ፡ የሚያርፍበት
ሃዘን ፡ ከኔ ፡ ርቆ ፡ ደስታን ፡ የማገኘው
ዐይኖቼን ፡ አንስቼ ፡ መስቀልህን ፡ ሳይ ፡ ነው

አዝ፦ ዐይኖቼን ፡ ከመስቀልህ ፡ አንስቼ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ (፪x)

ዐይኔን ፡ የጣልኩበት ፡ ከመስቀልህ ፡ ሌላ
ዘለቄታ ፡ የሌለው ፡ ጠፊ ፡ ነው ፡ በኋላ
ዓለሙም ፡ ምኞቱም ፡ ሁሉም ፡ ያልፋልና
እርዳኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በአንተ ፡ እንድፀና

አዝ፦ ዐይኖቼን ፡ ከመስቀልህ ፡ አንስቼ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ (፪x)

መብዛት ፡ ማነስንም ፡ በአንተ ፡ ተምሬአለሁ
ከአንተ ፡ ተለይቼ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ሰላም ፡ በበዛበት ፡ በቤትህ ፡ ተጥዬ
አንተን ፡ እጠብቃለሁ ፡ መስቀልህ ፡ ስር ፡ ሆኜ

አዝ፦ ዐይኖቼን ፡ ከመስቀልህ ፡ አንስቼ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ (፪x)

ልቆጥረው ፡ የማልችል ፡ ብዙ ፡ ውለህልኛል
ልለይህ ፡ አልችልም ፡ ፍቅር ፡ ግር ፡ ይለኛል
ደካማ ፡ ብሆንም ፡ ፀጋህ ፡ ይበቃኛል
ዘወትር ፡ በአንተ ፡ መኖር ፡ እጅግ ፡ ያረካኛል

አዝ፦ ዐይኖቼን ፡ ከመስቀልህ ፡ አንስቼ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፡ ከአንተ ፡ ርቄ (፪x)