አዬ ፡ ብቸኛው ፡ ብቸኛው (Ayie Bechegnaw Bechegnaw)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አዬ! ብቸኛው ፡ አዬ! ብቸኛው
ስለ ፡ በደሌ ፡ ሲል ፡ ሆነ ፡ ብቸኛ ፡ ሰው

መልክ ፡ ውበቱን ፡ አጥቶ ፡ መድኅኔ
ተዋረደ ፡ ለማልጠቅመው ፡ ለእኔ
ውለታ ፡ ዋለልኝ ፡ የማልረሳው
ትዝ ፡ የሚለኝ ፡ ከልቤ ፡ የማይጠፋው

አዝ፦ አዬ! ብቸኛው ፡ አዬ! ብቸኛው
ስለ ፡ በደሌ ፡ ሲል ፡ ሆነ ፡ ብቸኛ ፡ ሰው

መልክ ፡ ውበቱን ፡ አጥቶ ፡ መድኅኔ
ለጠፋሁት ፡ ተዋረደ ፡ ለእኔ
ተጓዘልኝ ፡ መስቀል ፡ ተሸክሞ
ተራራውን ፡ ወጣው ፡ ለእኔ ፡ ደክሞ

አዝ፦ አዬ! ብቸኛው ፡ አዬ! ብቸኛው
ስለ ፡ በደሌ ፡ ሲል ፡ ሆነ ፡ ብቸኛ ፡ ሰው

መልክ ፡ ውበቱን ፡ አጥቶ ፡ መድኅኔ
ተዋረደ ፡ ለማልጠቅመው ፡ ለእኔ
ብቸኝነት ፡ ስለእኔ ፡ አጥቅቶታል
ብርድም ፡ ውርጭም ፡ ጌታዬን ፡ ጐድቶታል

አዝ፦ አዬ! ብቸኛው ፡ አዬ! ብቸኛው
ስለ ፡ በደሌ ፡ ሲል ፡ ሆነ ፡ ብቸኛ ፡ ሰው

መልክ ፡ ውበቱን ፡ አጥቶ ፡ መድኅኔ
ጉስቁልና ፡ ቀመሰ፡ ስለእኔ
በምድር ፡ ተፈትኗል ፡ አለኝታዬ
ነፍሱን ፡ ሰጥቷል ፡ ስለእኔ ፡ ጌታዬ

አዝ፦ አዬ! ብቸኛው ፡ አዬ! ብቸኛው
ስለ ፡ በደሌ ፡ ሲል ፡ ሆነ ፡ ብቸኛ ፡ ሰው