አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ክንዱን ፡ አንስቶ (Ayehu Gietayie Kendun Anseto)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ክንዱን ፡ አንስቶ
የጠላቴን ፡ ራስ ፡ ሲቀጠቅጠው
አስርአቴንም ፡ ሲበጣጥሰው
ሞት ፡ ሞት ፡ የሸተተውን ፡ ሕይወት
በአዲስ ፡ መዓዛ ፡ ሲለውጠው

አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ዐይኔን ፡ ከፍቶ
የምህረት ፡ እጁን ፡ ተዘርግቶ
የማዳን ፡ ክንዱን ፡ አንስቶ
ተስፋ ፡ የቆረጠን ፡ አጽናንቶ
የደከመን ፡ እምነት ፡ አጽንቶ
ወደ ፡ መንጋ ፡ በረት ፡ መልሶ

አዝ፦ አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ክንዱን ፡ አንስቶ
የጠላቴን ፡ ራስ ፡ ሲቀጠቅጠው
አስርአቴንም ፡ ሲበጣጥሰው
ሞት ፡ ሞት ፡ የሸተተውን ፡ ሕይወት
በአዲስ ፡ መዓዛ ፡ ሲለውጠው

አማኑኤልን ፡ አየሁኝ
የጥልን ፡ ግድግዳ ፡ ሲያፈርስልኝ
ከአባቱ ፡ ጋር ፡ ሲያስታርቀኝ
ከብዶኝ ፡ የነበረውን ፡ ሲያነሳልኝ
የዛለ ፡ ሕይወቴን ፡ ሲያድስልኝ
የናዝሬቱን ፡ ኢየሱስን ፡ አንግሱልኝ

አዝ፦ አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ክንዱን ፡ አንስቶ
የጠላቴን ፡ ራስ ፡ ሲቀጠቅጠው
አስርአቴንም ፡ ሲበጣጥሰው
ሞት ፡ ሞት ፡ የሸተተውን ፡ ሕይወት
በአዲስ ፡ መዓዛ ፡ ሲለውጠው

ነውር ፡ ነቀፋዬን ፡ ደመሰሰው
የሃዘን ፡ ማቄን ፡ አወለቀው
ኀጢአቴን ፡ ሁሉ ፡ ባሕር ፡ ጣለው
መተላለፌን ፡ ደመሰሰልኝ
ህሊናዬንም ፡ አነጻልኝ
አጥቦ ፡ አድሶ ፡ ቀደሰልኝ

አዝ፦ አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ክንዱን ፡ አንስቶ
የጠላቴን ፡ ራስ ፡ ሲቀጠቅጠው
አስርአቴንም ፡ ሲበጣጥሰው
ሞት ፡ ሞት ፡ የሸተተውን ፡ ሕይወት
በአዲስ ፡ መዓዛ ፡ ሲለውጠው

አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ሲመጣልኝ
የትንሳኤ ፡ ሃይል ፡ ሲያውድልኝ
የደከመ ፡ ጉልበቴን ፡ ሲያድስልኝ
የደስታ ፡ ዘይት ፡ ሲያፈስልኝ
የማያቋርጥ ፡ ሰላም ፡ ሲያወርድልኝ
የደረቀ ፡ ሕይወቴን ፡ ሲያፍታታልኝ

አዝ፦ አየሁ ፡ ጌታዬ ፡ ክንዱን ፡ አንስቶ
የጠላቴን ፡ ራስ ፡ ሲቀጠቅጠው
አስርአቴንም ፡ ሲበጣጥሰው
ሞት ፡ ሞት ፡ የሸተተውን ፡ ሕይወት
በአዲስ ፡ መዓዛ ፡ ሲለውጠው