አያለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ዕርገትህን (Ayalehu Eyesus Ergetihin)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አያለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ዕርገትህን
ስታርግ ፡ ከምድራችን
እኔ ፡ ግን ፡ እንደ ፡ እንግዳ
ልኖር ፡ በውርደት ፡ ገና
ኅዘን ፡ ድካም ፡ ተከተለኝ
ገና ፡ ከአባቴ ፡ ቤት ፡ ሩቅ ፡ ነኝ

ያን ፡ ክቡር ፡ አገር ፡ በዕምነት
አሁንም ፡ ልመለከት
ከኃጢአቴ ፡ ተፈትቼ
ልከብር ፡ በጌታዬ
ልኖር ፡ ከብጹዓን ፡ ጋራ
በሕያው ፡ አምላክ ፡ ከተማ

በወዲያ ፡ የለም ፡ ሌሊት
ጨለማ ፡ ሐዘን ፡ ጭንቀት
በዚያ ፡ አለ ፡ መዝገቤ
በዚያም ፡ ይሁን ፡ ልቤ
ከኢየሱስ ፡ ይኑረኝ ፡ ኅብረት
ፀጋ ፡ ይስጠኝ ፡ ልኖርለት

ወደ ፡ ሰማይ ፡ እንደ ፡ ወጣ
ሊመለስ ፡ ወደ ፡ እኛ
ለሥራዬ ፡ እንድቀና
በጸሎት ፡ እንድተጋ
እስኪመጣ ፡ ባልታሰበው
ዕለት ፡ ዕለት ፡ ልጠብቀው

ትጉ ፡ ሎሌ ፡ በሚሠራ
ብጹዕ ፡ ነው ፡ ስትመጣ
ተስፋ ፡ ሰጠህ ፡ እንደሚወርስ
ያን ፡ ሰማያዊ ፡ መንግሥት
ልታድለው ፡ ክብረት ፡ ደስታ
በልዑል ፡ አባትህ ፡ ግርማ