Classics/Awon Gietayie Enie Anten Tamegnie

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዎን ፡ ጌታዬ ፡ እኔ ፡ አንተን ፡ ታምኜ (Awon Gietayie Enie Anten Tamegnie)

ከሆድ ፡ ያነሳኸኝ ፡ ከማህጸን ፡ የተሸከምከኝ
እስከ ፡ ሽምግልና ፡ የማትተወኝ
እስከ ፡ ሽበት ፡ የምትይዘኝ

አዝ፦ አዎን ፡ ጌታዬ
እኔ ፡ አንተን ፡ ታምኜ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ሆኜ (፪x)

በሞት ፡ ጥላ ፡ ብሄድ ፡ ብቀመጥም ፡ በጠላት ፡ መሃል
አንተን ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አልፈራም
ጠላቴም ፡ አያገኘኝም

አዝ፦ አዎን ፡ ጌታዬ
እኔ ፡ አንተን ፡ ታምኜ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ሆኜ (፪x)

ጠላቶቼ ፡ እንደ ፡ እልፍ ፡ እንደ ፡ አሸዋ ፡ ቢበረክቱም
ትታደገኝ ፡ ዘንድ ፡ በቀኜ ፡ አለህ
የእሳት ፡ ነበልባልን ፡ ለብሰህ

አዝ፦ አዎን ፡ ጌታዬ
እኔ ፡ አንተን ፡ ታምኜ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ሆኜ (፪x)

እናት ፡ ልጇን ፡ እስከማትራራ ፡ ትረሳ ፡ ይሆናል
አንተ ፡ ግን ፡ ፈጽሞ ፡ አትረሳኝም
ከእቅፍህ ፡ አታወጣኝም

አዝ፦ አዎን ፡ ጌታዬ
እኔ ፡ አንተን ፡ ታምኜ ፡ ኧረ ፡ ምን ፡ ሆኜ (፪x)