አሸናፊ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ (Ashenafi New Gietayie Eyesus)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ሁሉን ፡ ይረታል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (፪x)

የፅዮን ፡ አምባ ፡ የነፍሴ ፡ ንጉሥ
መች ፡ ትመጣለህ ፡ እስከዚያው ፡ ልታገሥ
የበጉ ፡ ሠርግም ፡ ተዘጋጅቶላታል
ነፍሴ ፡ ልትከብር ፡ ጥቂት ፡ ቀን ፡ ቀርቷታል

አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ሁሉን ፡ ይረታል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (፪x)

ዘመድ ፡ ቢከፋ ፡ ቀናት ፡ ቢለወጡም
ወዳጅ ፡ ዘመድም ፡ ባንድነት ፡ ቢከዱም
አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ ብቻ ፡ እኔን ፡ አቁመኝ
ጐርፍ ፡ እንዳይወስደኝ ፡ በፀጋህ ፡ ደግፈኝ

አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ሁሉን ፡ ይረታል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (፪x)

በሕይወቴ ፡ ታይ ፡ ግለጽ ፡ ክንድህን
ፀጋህ ፡ ይትረፍረፍ ፡ አፍስስ ፡ ኃይልህን
በድንቅ ፡ በተዓምር ፡ ይታወቅ ፡ ስምህ
ለሕዝቡ ፡ ይገለጥ ፡ ያ ፡ ገናናው ፡ ክብርህ

አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ሁሉን ፡ ይረታል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (፪x)

በክንድህ ፡ አቅፈህ ፡ ለዘለዓለም ፡ ልረፍ
በቃህ ፡ መከራ ፡ ዓለምን ፡ አሸነፍህ
የሚል ፡ ድምጽህን ፡ መቼ ፡ እሰማለሁ?
እስክትመጣልኝ ፡ እጠብቅሃለሁ

አዝ፦ አሸናፊ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ኢየሱስ (፪x)
ሁሉን ፡ ይረታል ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነው (፪x)