ዓርነት ፡ ወጣሁኝ ፡ በኢየሱሴ (Arinet Wottehugne BeEyesusie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዓርነት ፡ ወጣሁኝ
በኢየሱሴ
ከጭንቄም ፡ አረፍሁኝ
በ መ ድ ኃ ኒ ቴ  !
የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ደም
ጥቅሙን ፡ ክብሩንም
ቀድሞ ፡ አላወቅሁም
አሁን ፡ ታይቶኛል

የፀጋው ፡ ምሥጢሩ
ተገለጠ
አምላክ ፡ በፍቅሩ
ልጁን ፡ ለወጠ
ፍርድ ፡ ሲያስጨንቀኝ
ልቤም ፡ ሲያውከኝ
በእርሱ ፡ ሰላም ፡ አለኝ
በ መ ድ ኃ ኒ ቴ  !

ምን ፡ ያህል ፡ ደስታ
አለኝ ፡ አሁን
ከአምላኬ ፡ ይቅርታ
ምን ፡ ይበልጥ ፡ ይሆን?
ብዙ ፡ ቢጐድለኝም
አያስፈርድብኝም
ፍርድ ፡ አይደርስብኝም
በ መ ድ ኃ ኒ ቴ  !

እስከምሞት ፡ ልመን
በኢየሱስ ፡ ደም
ይምጣ ፡ የፍርድም ፡ ቀን
አያስፈራኝም
በኢየሱስ ፡ ችሮታ
የሰማይ ፡ ደስታ
አለኝ ፡ አለኝታ
በ መ ድ ኃ ኒ ቴ  !