አቀበቱን ፡ እወጣለሁ (Aqebetun Ewetalehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አቀበቱን ፡ እወጣለሁ
በየቀኑም ፡ አዘግማለሁ
እየጸለይሁ ፡ እጓዛለሁ
አምላክ ፡ ሆይ!
አዝልቀኝ ፡ እያልሁ

አዝ ፤
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ና ! አቁመኝ
በሰማይ ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ
አምላኬ ፡ ደኅና ፡ አዝልቀኝ
ከላይኛው ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ

ፍርሃትና ፡ ጥርጥርም
ካለበት ፡ ቦታ ፡ አልኖርም
ሌሎች ፡ ቢኖሩ ፡ ያን ፡ ወደው
የእኔ ፡ ምኞት ፡ በላይ ፡ ይሁን

አዝ ፤
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ና ! አቁመኝ
በሰማይ ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ
አምላኬ ፡ ደኅና ፡ አዝልቀኝ
ከላይኛው ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ

ዓለምን ፡ አሸንፋለሁ
ከሰይጣንም ፡ አመልጣለሁ
በሃይማኖት ፡ ይሰማኛል
መላዕክት ፡ ሲዘምሩ ፡ ሳለ

አዝ ፤
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ና ! አቁመኝ
በሰማይ ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ
አምላኬ ፡ ደኅና ፡ አዝልቀኝ
ከላይኛው ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ

እላይ ፡ ለመድረስ ፡ እሻለሁ
የክብሩን ፡ ብርሃን ፡ አያለሁ
ግን ፡ ከዚያ ፡ ላይ ፡ እስከምደርስ
አምላክ ፡ ከእኔ ፡ አትመለስ

አዝ ፤
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ና ! አቁመኝ
በሰማይ ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ
አምላኬ ፡ ደኅና ፡ አዝልቀኝ
ከላይኛው ፡ ሜዳ ፡ አድርሰኝ