From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በኃያል ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ
ከፍ ፡ በል ፡ ጌታችን ፡ ክብርህ ፡ ያስተጋባ
ቀድሰን ፡ በደምህ ፡ ምራ ፡ ይህን ፡ ስብሰባ
ታላቅነትህን ፡ እንየው ፡ እባክህ
አብራ ፡ መብራትህን ፡ ያንጸባርቅ ፡ ሞገስህ
አዝ፦ ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በኃያል ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ
ሥራ ፡ አምላካችን ፡ ክንድህም ፡ ይዘርጋ
በበደላችን ፡ ጦስ ፡ በርህን ፡ አትዝጋ
በያንዳንዳችን ፡ ልብ ፡ ኢየሱስ ፡ ተመላለስ
ስብሰባችንን ፡ ባርክ ፡ ፊትህንም ፡ መልስ
አዝ፦ ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በኃያል ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ
ባሪያህንም ፡ ባርከው ፡ ቃልህን ፡ ይናገር
በውስጡ ፡ ገስጸን ፡ ምስክርህንም ፡ይንገር
በሕዝብህ ፡ ፊት ፡ ቆሞ ፡ ደግሞ ፡ ለሚመራው
ፀጋህን ፡ አብዛለት ፡ በረከትህን ፡ ሙላው
አዝ፦ ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በኃያል ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ
መዘምራንን ፡ ባርክ ፡ በደምህ ፡ ከልለህ
ለሕዝብህ ፡ በረከት ፡ ይዋሉ ፡ ለክብርህ
የሚዘምሩትን ፡ ለክብርህ ፡ አውለው
ለክርስቲያን ፡ ሁሉ ፡ ክንድህ ፡ እንዲታየው
አዝ፦ ጌታ ፡ አምላካችን ፡ አንተው ፡ ሥራበት
በኃያል ፡ ክንድህ ፡ ተመላለስበት
ጐስቋላነታችንን ፡ በደምህ ፡ ሸፍነህ
በዚህ ፡ ሥፍራ ፡ ክበር ፡ ስለ ፡ ስምህ
|