From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ባዶ ፡ የቀረ
መከራ ፡ ገጥሞት ፡ የተማረረ
አላየሁኝም ፡ አልሰማሁኝም
ባለፈው ፡ ዘመን ፡ ታሪክ ፡ የመርመር ፡ ከቶ ፡ አይገኝም
አዝ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲኛው ፡ ዓለም
ሥጋ ፡ ለባሹን ፡ የተደገፈ
በሰው ፡ ስራ ፡ ላይ ፡ ዐይኑ ፡ ያረፈ
ምርኩዙ ፡ ሲወድቅ ፡ እርሱም ፡ ወደቀ
አንተን ፡ ያለው ፡ ግን ፡ የማታ ፡ ማታ ፡ ደስ ፡ ብሎት ፡ ሳቀ
አዝ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲኛው ፡ ዓለም
እኔም ፡ በዓለፈው ፡ ሰውን ፡ አይቼ
ተጐድቻለሁ ፡ መንገዴን ፡ ስቼ
ከእንግዲህ ፡ አንተን ፡ እጠብቃለሁ
ዛሬ ፡ ባለቅስም ፡ የማታ ፡ ማታ ፡ እኔ ፡ እስቃለሁ
አዝ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲኛው ፡ ዓለም
የእምባዬም ፡ ፍሬ ፡ ለምልሞ ፡ ባላይ
ቢያጠወልገው ፡ የበጋው ፡ ፀሐይ
የመጨረሻው ፡ ዝናብ ፡ ይዘንባል
የእኔም ፡ ፈተና ፡ ከነኮተቱ ፡ ገደል ፡ ይገባል
አዝ፦ አንተን ፡ መጠበቅ ፡ ብዙ ፡ ትርፍ ፡ አለው
ለታገሰ ፡ ሰው ፡ ፀጋህ ፡ ላስቻለው
አንተን ፡ ጠብቆ ፡ ያፈረ ፡ የለም
በዚህ ፡ ምድር ፡ ይሁን ፡ በወዲኛው ፡ ዓለም
|