From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አንተን ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እሻለሁ
እኔ ፡ ጥፋተኛ ፡ ነኝ
ያለ ፡ አንተም ፡ እጠፋለሁ
ያለ ፡ አንት ፡ የሞትሁም ፡ ነኝ
ቅዱስ ፣ ክቡር ፡ ደምህ ፡ ብቻ
ሊያጠራኝ ፡ ይችላል
የአንተ ፡ ጽድቅ ፣ የአንተም ፡ ይቅርታ
እኔንም ፡ ያጸድቀኛል
አንተን ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እሻለሁ
እኔ ፡ ራሴ ፡ ዕውር ፡ ነኝ
ወትሮ ፡ እንከራተታለሁ
መንገዱንም ፡ አላገኝ
ና ፡ በዕውነትህ ፡ ብርሃንም
እጄንም ፡ ይዘህ ፡ ምራኝ
በአንተ ፡ ጽድቅ ፡ በአንተ ፡ ሥልጣንም
ወደ ፡ መንግሥትህ ፡ አግባኝ
አንተን ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እሻለሁ
በዚህ ፡ ስደተኛ ፡ ነኝ
ርስት ፡ በላይ ፡ ተቀብያለሁ
አንተ ፡ ራስህ ፡ ሰጠኸኝ
ወደዚያም ፡ እጓዛለሁ
መንገዴም ፡ ሸካራ ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ ሆይ! አንተን ፡ እሻለሁ
ኃይልህ ፡ ብቻ ፡ ኃይሌ ፡ ነው
አንተን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እሻለሁ
በደለእኛን ፡ የሚችል
አንድ ፡ ወዳጅ ፡ እፈልጋለሁ
ክፉውንም ፡ የማይጥል
አንተም ፡ ሠርክ ፡ ትወደኛለህ
አንተ ፡ አትጥለኝም
ጉድለቴንም ፡ ታውቃለህ
ፍቅርህ ፡ ግን ፡ አይተወኝም
አንተን ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እሻለሁ
በፈቃድህም ፡ ምራኝ
መንፈስህንም ፡ እሻለሁ
እርሱን ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ምላኝ
እርሱ ፡ ትልቅ ፡ ኃጢአቴን
ሁሉ ፡ ቀን ፡ ያሳስበኝ
እርሱም ፡ የሥርየት ፡ ብዛትን
በአንተ ፡ ቃል ፡ ያስተምረኝ
በምድራዊ ፡ ሕይወት ፡ ሳለሁ
ሲያልቅብኝም ፡ ቀኔ
አንተን ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እሻለሁ
እንድድን ፡ ከኩነኔ
አንድ ፡ ዕርምጃ ፡ ለመራመድ
ያለ ፡ አንተ ፡ አልችልም
ከእኔ ፡ ጋር ፡ ግን ፡ ብትዛመድ
አንዳችም ፡ አይጐድለኝም
አንተን ፣ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ እሻለሁ
አንተ ፡ ብቻ ፣ ሃብቴ ፡ ነህ
አንተንም ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ አይሃለሁ
በዓብ ፡ ቀኝ ፡ ተቀምጠህ
ወደ ፡ ጽዮንም ፡ ተራራ
አድነህ ፡ ስታደርሰኝ
ደምህ ፡ ከገዛቸው ፡ ጋራ
ክብርህን ፡ ልዘምር ፡ ነኝ
|