አንተን ፡ ብለን ፡ መጣን (Anten Belen Metan)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አንተን ፡ በለን ፡ መጣን ፡ ሁሉን ፡ ትተን
መረባችንን ፡ ከወንዙ ፡ ዳር ፡ ጥለን
ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይሻለናል ፡ ብለን
ከጊዜያዊው ፡ የዘለዓለሙን ፡ መርጠን
ይኸው ፡ መጣን ፡ አንተን ፡ ተከትለን (፪x)

እንደ ፡ አህዛብ ፡ አዕምሮ ፡ ከንቱነት
ስንወጣ ፡ ስንገባ ፡ ያለ ፡ እረፍት
በመስቀልህ ፡ ሰማይ ፡ ምድር ፡ ታርቀው
ደህንነት ፡ ታወጀ ፡ ተቀራርበው

አዝ፦ አንተን ፡ በለን ፡ መጣን ፡ ሁሉን ፡ ትተን
መረባችንን ፡ ከወንዙ ፡ ዳር ፡ ጥለን
ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይሻለናል ፡ ብለን
ከጊዜያዊው ፡ የዘለዓለሙን ፡ መርጠን
ይኸው ፡ መጣን ፡ አንተን ፡ ተከትለን (፪x)

በድንቅም ፡ አጠራሩም ፡ እሱ ፡ ጠራን
መረብ ፡ ታንኳችንን ፡ ጥለን ፡ መጣን
ሕይወት ፡ ሆኖ ፡ ለእኛ ፡ ሕይወት ፡ ሰጠን
ያየነውን ፡ እኛም ፡ እናወራለን

አዝ፦ አንተን ፡ በለን ፡ መጣን ፡ ሁሉን ፡ ትተን
መረባችንን ፡ ከወንዙ ፡ ዳር ፡ ጥለን
ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይሻለናል ፡ ብለን
ከጊዜያዊው ፡ የዘለዓለሙን ፡ መርጠን
ይኸው ፡ መጣን ፡ አንተን ፡ ተከትለን (፪x)

የተሰጠንን ፡ አደራ ፡ ጥለን
በገሊላ ፡ ባሕር ፡ ዳር ፡ ተቀምጠን
ሌሊቱን ፡ ስንለፋ ፡ ባዶ ፡ አድርገን
ተስፋ ፡ ቆርጠን ፡ ሳለ ፡ ጌታ ፡ አገኘን

አዝ፦ አንተን ፡ በለን ፡ መጣን ፡ ሁሉን ፡ ትተን
መረባችንን ፡ ከወንዙ ፡ ዳር ፡ ጥለን
ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይሻለናል ፡ ብለን
ከጊዜያዊው ፡ የዘለዓለሙን ፡ መርጠን
ይኸው ፡ መጣን ፡ አንተን ፡ ተከትለን (፪x)

የዛሬ ፡ መከራ ፡ ሳይበግረን
ብድራችንን ፡ በእምነት ፡ አይተን
በአንተ ፡ መኖር ፡ ይሻለናል ፡ ብለን
ጉዞ ፡ ጀመርን ፡ አንተን ፡ ተከትለን

አዝ፦ አንተን ፡ በለን ፡ መጣን ፡ ሁሉን ፡ ትተን
መረባችንን ፡ ከወንዙ ፡ ዳር ፡ ጥለን
ከሞት ፡ ሕይወት ፡ ይሻለናል ፡ ብለን
ከጊዜያዊው ፡ የዘለዓለሙን ፡ መርጠን
ይኸው ፡ መጣን ፡ አንተን ፡ ተከትለን (፪x)