አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ (Ante Talaq Neh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በዘመናችን ፡ በዓለም ፡ ሁሉ
ከቁጥር ፡ በላይ ፡ አማልክት ፡ አሉ
ተወዳዳሪ ፡ አቻ ፡ የሌለህ
እውነተኛ ፡ አምላክ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ

አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
ትልቅ ፡ እድል ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ መጠራት
በአህዛብ ፡ መኻል ፡ ስራህን ፡ ማውራት

በፍልስፍና ፡ ባሕር ፡ ውስጥ ፡ ገብቶ
አድኑኝ ፡ አይል ፡ አይወጣ ፡ ዋኝቶ
የሞት ፡ ጦር ፡ ይዞት ፡ ይንፈራገጣል
ባረረ ፡ ምላስ ፡ ጌታ ፡ የለም ፡ ይላል

አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
ትልቅ ፡ እድል ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ መጠራት
በአህዛብ ፡ መኻል ፡ ስራህን ፡ ማውራት

ጣፋጭነት ፡ ስለቀመስኩኝ
በእምነት ፡ እጆችህ ፡ ስለዳሰሰኝ
የለም ፡ ብትባት ፡ አለህ ፡ እላለሁ
ለስምህም ፡ ክብር ፡ እዘምራለሁ

አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
ትልቅ ፡ እድል ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ መጠራት
በአህዛብ ፡ መኻል ፡ ስራህን ፡ ማውራት

አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ የማትረታ
የተዋጊውን ፡ ቀንድ ፡ የምትመታ
በአንበሳው ፡ አፍ ፡ ልጓም ፡ አድርገህ
ጠብቀኸኛል ፡ ጓዳ ፡ ሸሽገህ

አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
ትልቅ ፡ እድል ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ መጠራት
በአህዛብ ፡ መኻል ፡ ስራህን ፡ ማውራት

አዩኝ ፡ አላዩኝ ፡ መሸማቀቄ
ከሰው ፡ ሳያንሱ ፡ በሰው ፡ መናቄ
ይሁን ፡ ግድ ፡ የለም ፡ ፀሐይ ፡ ይወጣል
የተሰወረው ፡ ሁሉ ፡ ይገለጣል

አዝ፦ አንተ ፡ ታላቅ ፡ ነህ ፡ ለዘለዓለም
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ድንቅ ፡ አምላክ ፡ የለም
ትልቅ ፡ እድል ፡ ነው ፡ በአንተ ፡ መጠራት
በአህዛብ ፡ መኻል ፡ ስራህን ፡ ማውራት