አንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (Ante Mesganayie Neh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝአንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዓመታት
አንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዘመናት

1. ክፉ ፡ ሲመጣ ፡ ያመለጥኩብህ
ስጣል ፡ ስረሳ ፡ የታቀፍኩብህ
በአንተ ፡ እዚህ ፡ ደረስኩ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ሆነህ
ኢየሱስ ፡ ለእኔ ፡ ምስጋናዬ ፡ ነህ

አዝአንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዓመታት
አንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዘመናት

2. አይኔ ፡ አየችህ ፡ አትደክምም ፡ በእኔ
ባልመችህም ፡ ሰው ፡ በመሆኔ
ምሥጋናን ፡ ላውጅ ፡ በቤትህ ፡ ዙሪያ
ነፍሴ ፡ ትባርክህ ፡ ቆማ ፡ እንደገና

አዝአንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዓመታት
አንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዘመናት

3. በጠላቴ ፡ ፊት ፡ ሞገስ ፡ ሆንክልኝ
በእሳት ፡ መካከል ፡ አደላደልከኝ
በአንተ ፡ ተደገፍኩ ፡ ምርኩዝ ፡ ሆንክልኝ
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክልኝ

አዝአንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዓመታት
አንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዘመናት

4. በድካም ፡ ጐኔ ፡ አንተ ፡ ቆምክልኝ
ጠላቴን ፡ ታግለህ ፡ አሸነፍክልኝ
የት ፡ ያገኘኛል ፡ ተሻግሬአለሁ
ከአንተ ፡ የተነሳ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አለሁ

አዝአንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዓመታት
አንተ ፡ ምሥጋናዬ ፡ ነህ (፫) ለዘመናት