From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ኀጢአቴን ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ቁስሎቹ ፡ ስር ፡ ሸሸገልኝ
ቆልጭ ፡ አድርጐ ፡ አሳይቶ ፡ በደሌን ፡ ደመሰሰልኝ
አሁን ፡ ይቅር ፡ ተብያለሁ ፡ ምህረቱንም ፡ አግኝቻለሁ
ለኃጢአት ፡ ሁሉ ፡ ሞቻለሁ
ለጽድቅም ፡ ደግሞ ፡ እቆማለሁ ፡ ወደ ፡ ኢየሱስ ፡ እገባለሁ
ሕያው ፡ ሆኜ ፡ እኖራለሁ
አዝ፦ አንተ ፡ ለእኔ ፡ ውበቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ሞገሴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ሕይወቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ብርሃኔ ፡ ነህ ፡ መስታወቴ ፡ የምታሳየኝ ፡ ጉድለቴን
ቁልጭ ፡ አድርገህ ፡ አሳይተህ ፡ ምታነሳ ፡ ቆሻሻዬን
መስቀል ፡ ላይ ፡ በፈሰሰው ፡ ደሙ ፡ በችንካሩ ፡ ጠግኖኛል
ኢየሱስ ፡ በግርፋቱ ፡ በቁስሎቹ ፡ ፈውሶኛል
ኧረ ፡ ማነው ፡ በዚህ ፡ ምድር ፡ የጠላት ፡ ፍቅር ፡ ገዶት
ደገፍ ፡ አድርጐ ፡ ያስታመመው
የቀራንዮው ፡ ባለውለታ ፡ እርሱ ፡ እርሱ ፡ ፍቅር ፡ የሆነው
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው
አዝ፦ አንተ ፡ ለእኔ ፡ መድሃኒቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ፈዋሼ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ሃኪሜ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ስታመም ፡ አብረኸኝ ፡ ታመህ ፡ ስጨነቅ ፡ አብረህ ፡ ተጨንቀህ
ሳትሰለች ፡ ደገፍ ፡ አድርገህ ፡ ምታስቆመኝ ፡ ቀና ፡ አድርገህ
ከማንም ፡ ይልቅ ፡ ምትወደኝ ፡ ሚስጥረኛዬ ፡ አንተ ፡ ነህ
ከእናት ፡ ከአባት ፡ ከእህት ፡ ወንድም ፡ ከወገን ፡ ዘመድ ፡ ትበልጣለህ
እንዳንተ ፡ ሚሆነኝ ፡ የለም ፡ ለሞቴና ፡ ለሕይወቴ
ለሥጋም ፡ ቢሆን ፡ ለነፍሴ
ጐዳናዬ ፡ መንገዴ ፡ ነህ ፡ መነሻና ፡ መድረሻዬ
አንተ ፡ ነህ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
አዝ፦ አንተ ፡ ለእኔ ፡ አባቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ እናቴ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ወገኔ ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ለእኔ
አንተ ፡ ለእኔ ፡ ወዳጅ ፡ ዘመድ ፡ አዝማዴ ፡ ነህ ፡ የምትቀርበኝ ፡ ጓደኛዬ
ችግሬን ፡ ምትረዳልኝ ፡ የምታውቅልኝ ፡ ጓዳዬን
|