አንተ ፡ እየመራኸን (Ante Eyemerahen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አንተ ፡ እየመራኸን ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል
ክፉውንም ፡ ዘመን ፡ በአንተ አልፈናል
የነገንም ፡ ደግሞ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ
አንተ ፡ በተዐምራት ፡ ታከርመናለህ ፡ ታኖረናለህ

በእጃችን ፡ ያለው ፡ ጥቂት ፡ ዲቄት ፡ ነው ፡ ጥቂት ፡ ዘይት ፡ ነው
ያቺኑ ፡ በልተን ፡ ለነገ ፡ ደግሞ ፡ አንተን ፡ ማየት ፡ ነው
ግን ፡ አንተ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
የተራበን ፡ ነፍስ ፡ አንተ ፡ አጥግበሃል (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ እየመራኸን ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል
ክፉውንም ፡ ዘመን ፡ በአንተ አልፈናል
የነገውን ፡ ደግሞ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ
አንተ ፡ በተዐምራት ፡ ታከርመናለህ ፡ ታኖረናለህ

መንገድ ፡ ዳር ፡ ቁጭ ፡ አልኩ ፡ ጭንቀት ፡ ቢይዘኝ ፡ መፈወስ ፡ ቢያምረኝ
ከእውርነቴ ፡ ብትፈታኝ ፡ ብዬ ፡ ብትገላገለኝ
አውቃለሁ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ ይሳንሃል
የእውሩን ፡ ዐይኖች ፡ አንተ ፡ አብርተሃል (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ እየመራኸን ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል
ክፉውንም ፡ ዘመን ፡ በአንተ አልፈናል
የነገንም ፡ ደግሞ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ
አንተ ፡ በተዐምራት ፡ ታከርመናለህ ፡ ታኖረናለህ

ከባዕድ ፡ ምድር ፡ አንተ ፡ አወጣኸኝ ፡ ለዚህ ፡ አደረከን
ወጉን ፡ ማዕረጉን ፡ በአንተ ፡ ውስጥ ፡ ሆነን ፡ ሁሉንም ፡ አየን
ታዲያ ፡ ለነገ ፡ ምን ፡ ያስፈራናል
ኤልሻዳይ ፡ ጌታ ፡ አንተ ፡ ካለኸን (፪x)

አዝ፦ አንተ ፡ እየመራኸን ፡ እዚህ ፡ ደርሰናል
ክፉውንም ፡ ዘመን ፡ በአንተ አልፈናል
የነገንም ፡ ደግሞ ፡ አንተ ፡ ታውቃለህ
አንተ ፡ በተዐምራት ፡ ታከርመናለህ ፡ ታኖረናለህ