አንድ ፡ ወዳጅ ፡ በምሄድበት ፡ ሁሉ (And Wedaj Bemehiedebet Hulu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አንድ ፡ ወዳጅ ፡ በምሄድበት ፡ ሁሉ
ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ይመላለሳል
ላይኔ ፡ አይታይም ፡ ግን ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉ
ወደ ፡ ልቤ ፡ ይደርስልኛል
ያ ፡ ወዳጅ ፡ ስለእኔ ፡ ሞቶ ፡ ነበር
ከመቃብር ፡ ግን ፡ ተነሥቷል
እረኛችን ፡ ሆኖ ፡ በማይነገር
ርህራሄ ፡ ለመንጋው ፡ ያስባል

ሁልጊዜ ፡ የሚያስፈልገኝን
ቸር ፡ እረኛ ፡ ያቀርብልኛል
ልቤንም ፡ የሚያቆስለኝን
ፈውሶ ፡ ረድዔት ፡ ይሰጠኛል
አጭር ፡ ዘመን ፡ እንዲሰወርብኝ
እርሱ ፡ ራሱ ፡ ገልጦ ፡ ብሎኛል
ግን ፡ ተመልሶ ፡ ሲገለጥልኝ
ደስታና ፡ ሰላም ፡ ይሆነኛል

ድል ፡ የነሳ ፡ ዕሙኑ ፡ መድኃኒት
ቶማስ ፡ ሲጠረጥር ፡ አሰበው
እንዲሰጠውም ፡ ቅዱስ ፡ መጸናናት
ቁስሎቹን ፡ አመለከተው
ቶማስ ፡ ጌታን ፡ አውቆ ፡ አዲስ ፡ ተስፋ
ምሉ ፡ ዕምነትም ፡ ተቀብሎ
ጮኸ ፡ በማይነገር ፡ ቅዱስ ፡ ደስታ
ጌታዬና ፡ አምላኬ ፡ ብሎ

ለእኔ ፡ ደግሞ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆይ ፡ ራራልኝ
ያንን ፡ ደስታ ፡ አትከልክለኝ
አለማመኔም ፡ እንዲጠፋልኝ
ቁስሎችህን ፡ አሳስበኝ
ቸር ፡ እረኛ ፡ እኔ ፡ ምስኪን ፡ በግህ
ተስፋዬ ፡ በአንተ ፡ ብቻ ፡ ነው
አንተንም ፡ ኦ! አምላኬ ፡ የማውቅህ
ቁስልህን ፡ ስታሳየኝ ፡ ነው

የተወጋው ፡ ልብህ
ኦ! ቸር ፡ መድኅን
ያስበኝ ፡ በዓለም ፡ በረሃ
በዕምነትም ፡ ልመልከት ፡ ቁስልህን
በትካዜና ፡ በፍስሐ
ና ፡ አሳርፈኝ ፡ በርህሩህ ፡ ዕቅፍህ
አድርሰኝ ፡ ወደ ፡ ኢየሩሣሌም
ድኜም ፡ ፊት ፡ ለፊት ፡ ኦ! ጌታ ፡ ልይህ
ኦ! መድኃኒቴ ፡ ል! አምላኬም