አንድ ፡ ነን ፡ በመንፈሱ (And Nen Bemenfesu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አንድ ፡ ነን ፡ በመንፈሱ ፡ አንድ ፡ ነን ፡ በጌታ (፪x)
ይህንን ፡ ለማስታወቅ ፡ በፍቅር ፡ እንበርታ
አንድነታችንን ፡ አሕዛብ ፡ ያያሉ ፡ ያያሉ
በፍቅር ፡ አንድነታችንን ፡ ያውቃሉ

በአንድ ፡ መንፈስ ፡ ተጠምቀናል ፡ በአንድነት ፡ እንሄዳለን (፪x)
እርስ ፡ በርሳችን ፡ እንደባሮች ፡ በፍቅር ፡ እንሆናለን
አንድነታችንን ፡ አሕዛብ ፡ ያያሉ ፡ ያያሉ
በፍቅር ፡ አንድነታችንን ፡ ያውቃሉ

በአንድነት ፡ ተጠምደናል ፡ በአንድነት ፡ እንሠራለን (፪x)
የአምላካችንን ፡ ሕልውና ፡ ሁሌ ፡ እናወራለን
አንድነታችንን ፡ አሕዛብ ፡ ያያሉ ፡ ያያሉ
በፍቅር ፡ አንድነታችንን ፡ ያውቃሉ