አምላክን ፡ ወደማይፈሩ ፡ ያልተጠጋ ፡ ሰው (Amlakn Wodemayferu Yaltettega Sew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ዳዊት ፡ ፩
አምላክን ፡ ወደማይፈሩ
ያልተጠጋ ፡ ሰው ፡ ምሥጉን ፡ ነው
በክፎች ፡ ምክር ፡ ያልሄደ ፡ ሰው
በዋዘኞችም ፡ ወንበሮች ፡ ያልተቀመጠ
በአምላክ ፡ ሕግ ፡ ደስ ፡ የሚለው
ሕጉንም ፡ የሚያስብ ፡ በቀንና ፡ ሌት
እርሱ ፡ ነው ፡ እንደ ፡ ዛፍ ፡ የተተከለች
በውኃ ፡ ፈሳሽ ፡ ዳር ፡ በውኃ ፡ ፈሳሽ ፡ ዳር
በየጊዜዋ ፡ ፍሬዋን ፡ የምትሰጥ
ቅጠሏ ፡ አይረግፍም ።