From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አምላክህ ፡ ለፍርድ ፡ ቢመጣብህ ፡ አሁን
እንዴት ፡ ይሆንብህ ፡ ይሆን?
የፍርድ ፡ መለከጽ ፡ ቢሰማ ፡ አሁን?
ምን ፡ ሃሣብ ፡ ይይዝህ ፡ ይሆን?
እንዴትስ ፡ ያን ፡ ድምፅ ፡ ትሰማለህ?
ባላሰብኸው ፡ ወቅት ፡ በማይመስልህ ፡ ሰዓት
ያ ፡ ቀን ፡ እንደ ፡ ሌባ ፡ ይመጣል
ለቅዱሣን ፡ ደስታ ፣ ለኃጥአን ፡ ፍርሃት
ጌታችን ፡ በፍርዱ ፡ ይሰጣል
ለአንተስ ፡ ምን ፡ ይሰጥህ ፡ ይሆን?
በጐችን ፡ በቀኝ ፣ ፍየሎችን ፡ በግራ
አስቀምጦ ፡ መንጋውን ፡ ይለያል
አንተንስ ፡ ከበጐቹ ፡ ጋራ ፡ ይጥራ
ወይስ ፡ ሥፍራህን ፡ የት ፡ ላይ ፡ ያሳያል?
የት ፡ ላይ ፡ ትቆማለህ ፡ በፍርዱ?
በጐቹን ፡ በፍቅር ፣ እላንት ፡ ቡሩካን
እያለ ፡ በገነት ፡ ያስገባል
ለኃጥአን ፡ ግን ፣ ሂዱ! እላንት ፡ ርጉማን
ብሎ ፡ መቅሠፍታቸውን ፡ ይሰጣል
ለአንተስ ፡ ምን ፡ ይልህ ፡ ይሆን?
ከአምላክህ ፡ ጋር ፡ አሁን ፡ ተገናኝ
ኢየሱስን ፡ ለማወቅ ፡ ተጋደል
አሁን ፡ ለሁላችን ፡ ሥርየቱን ፡ ሲናኝ
ጊዜ ፡ ሳያልፍብህ ፡ ተቀበል
የፀጋን ፡ ጊዜ ፡ አታባክን!!
|