አምላኬ ፡ ወደ ፡ አንተ (Amlakie Wede Ante)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አምላኬ ፡ ወዳንተ
እቀርባለሁ
ሸክሜ ፡ እንኳ ፡ ቢከብድ
ከነሸክሜ ፡ አሁንም ፡ መዝሙሬ ፡ ወዳንተ
መቅረብ ፡ ነው ፡ ወዳንተ
መቅረብ ፡ ነው ፡ አምላኬ ፡ ሆይ !
ሳላስበው ፡ ቀኑ
ከንቱ ፡ ሄደ
ጨለማ ፡ ከበበኝ ፡ በበረሃ
በሕልም ፡ እንኳ ፡ ሆኜ
አምላኬ ፡ ወዳንተ
ወዳንተ ፡ እቀርባለሁ
የሰማይን ፡ መንገድ
ግለጥልኝ
በምሕረትህ ፡ ሁሉን ፡ ስደድልኝ
መላዕክትህ ፡ ያድሙኝ ፡ ጌታዬ
አምላኬ ፡ ወዳንተ
ወዳንተ ፡ እቀርባለሁ
በነቃ ፡ ሃሣቤ
ሳመሰግን
ከሃዘኔ ፡ ሥፍራ ፡ ቤቴን ፡ ልሥራ
ጩኸቴን ፡ ለማቅረብ ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ ወዳንተ
ወዳንተ ፡ እቀርባለሁ
ከዚህ ፡ በደስታ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ለመሄድ
በዕልልታ ፡ እበራለሁ
መዝሙሬን ፡ ስዘምር ፡ አምላኬ
አምላኬ ፡ ወዳንተ
ወዳንተ ፡ እቀርባለሁ
|