አምላኬ ፡ ድንቅ ፡ ያደረገላችሁ (Amlakie Denq Yaderegelachuh)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አምላኬ (አምላኬ)
ድንቅ ፡ ያደረገላችሁ ፡ በዝምታ
ማዳኑን ፡ ያያችሁ ፡ በዕልልታ ፡ በሆታ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ
አሕዛብ ፡ ሁሉ ፡ ይስሙ
ታምራቱን ፡ ያውሩ

1. በሰዎች ፡ ታይታችሁ ፡ ሥፍራ ፡ ያልነበራችሁ
እንደ ፡ ምናምንቴ ፡ የተቆጠራችሁ
ዛሬ ፡ ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ ከትቢያ ፡ ያወጣችሁ
ተነሡ ፡ አመስግኑት ፡ በአንድነት ፡ ሁላችሁ

አዝ፦ አምላኬ (አምላኬ)
ድንቅ ፡ ያደረገላችሁ ፡ በዝምታ
ማዳኑን ፡ ያያችሁ ፡ በዕልልታ ፡ በሆታ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ
አሕዛብ ፡ ሁሉ ፡ ይስሙ
ታምራቱን ፡ ያውሩ

2. በምህረት ፡ ይቅርታው ፡ የተደነቃችሁ
በፍቅሩ ፡ ደግፎ ፡ የተሸከማችሁ
ኑ ፡ በአንድነት ፡ ሆነን ፡ ሥሙን ፡ እናክብረው
ጌታ ፡ ሰው ፡ አድርጐናል ፡ ምሥጋና ፡ እንስጠው

አዝ፦ አምላኬ (አምላኬ)
ድንቅ ፡ ያደረገላችሁ ፡ በዝምታ
ማዳኑን ፡ ያያችሁ ፡ በዕልልታ ፡ በሆታ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ
አሕዛብ ፡ ሁሉ ፡ ይስሙ
ታምራቱን ፡ ያውሩ

3. የጨለማን ፡ ዘመን ፡ እርሱ ፡ ያሳለፋችሁ
ለቅሶአችሁን ፡ አይቶ ፡ ብርሃን ፡ ያሳያችሁ
ክብሩን ፡ ንገሩለት ፡ ለአሕዛብ ፡ በሙሉ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ ማንም ፡ የለም ! በሉ

አዝ፦ አምላኬ (አምላኬ)
ድንቅ ፡ ያደረገላችሁ ፡ በዝምታ
ማዳኑን ፡ ያያችሁ ፡ በዕልልታ ፡ በሆታ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ
አሕዛብ ፡ ሁሉ ፡ ይስሙ
ታምራቱን ፡ ያውሩ

4. ለእኛ ፡ ያላረገው ፡ ከቶ ፡ ምን ፡ አለና?
አፋችን ፡ ዝም ፡ አይበል ፡ አይከልክል ፡ ምሥጋና
ምንድን ፡ ነው ፡ ዝምታው ? እስኪ ፡ ዝም ፡ አትበሉ
ሴቶች ፡ ዕልል! በሉ ፡ ወንዶችም ፡ ሆ ! በሉ

አዝ፦ አምላኬ (አምላኬ)
ድንቅ ፡ ያደረገላችሁ ፡ በዝምታ
ማዳኑን ፡ ያያችሁ ፡ በዕልልታ ፡ በሆታ
ለእርሱ ፡ ዘምሩ
አሕዛብ ፡ ሁሉ ፡ ይስሙ
ታምራቱን ፡ ያውሩ