አምላክ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነው (Amlak Yenie Eregna New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አምላክ ፡ የእኔ ፡ እረኛ ፡ ነው
የሚያሳጣኝ ፡ የለም
ወደ ፡ ለመለመ ፡ መስክ
እርሱ ፡ ይመራኛል

አዝ፦ ይመራኛል ፣ ይመራኛል
ወደ ፡ ጥሩ ፡ ውኃ ፡ በለመለመ
መስክ ፡ ይመራኛል

ደካማ ፡ ነፍሴን ፡ ያሳርፋል
በጽድቅ ፡ መንገድ ፡ ይመራል
የልዑል ፡ ክንድ ፡ ያጸናኛል
በሥሙ ፡ ምክንያት

አዝ፦ ይመራኛል ፣ ይመራኛል
ወደ ፡ ጥሩ ፡ ውኃ ፡ በለመለመ
መስክ ፡ ይመራኛል

በሞት ፡ ጽላ ፡ ወንዝ ፡ ብሄድ
ምንም ፡ ክፉን ፡ አልፈራም
አንተ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ ፡ ከሆንህ
ጽናቴም ፡ ምርኩዝን

አዝ፦ ይመራኛል ፣ ይመራኛል
ወደ ፡ ጥሩ ፡ ውኃ ፡ በለመለመ
መስክ ፡ ይመራኛል

ገበታዬን ፡ አዘጋጀህ
በጠላቶቼ ፡ ፊት
ራሴን ፡ በዘይት ፡ ቀባኸው
ጽዋዬም ፡ ተርፏል

አዝ፦ ይመራኛል ፣ ይመራኛል
ወደ ፡ ጥሩ ፡ ውኃ ፡ በለመለመ
መስክ ፡ ይመራኛል

የአንተ ፡ ምሕረት ፡ ቸርነትም
እኔን ፡ ይከተላሉ
ለዘለዓለም ፡ እኖራለሁ
በልዑል ፡ አምላክ ፡ ቤት

አዝ፦ ይመራኛል ፣ ይመራኛል
ወደ ፡ ጥሩ ፡ ውኃ ፡ በለመለመ
መስክ ፡ ይመራኛል