አምላክ ፡ ለእኛ ፡ ብሎ ፡ ቢያፈሰው ፡ ደሙን (Amlak Legna Belo Biyafesew Demun)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. አምላክ ፡ ለእኛ ፡ ብሎ ፡ ቢያፈሰው ፡ ደሙን
ፀሐይ ፡ ከለከለች ፡ ደማቅ ፡ ብርሃንዋን
የከበረው ፡ ስጋ ፡ የከበረው ፡ ደም
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ዋለ ፡ ኢየሩሳሌም

አዝ፦ እዩት ፡ ኢየሱስን ፡ መስቀሉ ፡ ማማሩ
ለተመራመረው ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ

2. ቢመቱት ፡ ቢሰቅሉት ፡ ብያላግጡበት
ምንም ፡ አላገኙም ፡ በእርሱ ፡ ላይ ፡ ስህተት
ፈጣሪ ፡ መሆኑን ፡ ሚሰጥሩ ፡ ገብቷት
ጌታን ፡ አልይዝም ፡ አለች ፡ ጉዑዟ ፡ መሬት

አዝ፦ እዩት ፡ ኢየሱስን ፡ መስቀሉ ፡ ማማሩ
ለተመራመረው ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ

3. ይህ ፡ ታላቅ ፡ ንጉሥ ፡ ሲገለጥ ፡ በሰማይ
የናቁት ፡ የወጉት ፡ ይሉለታል ፡ ዋይ ፡ ዋይ
ምድርና ፡ ሰማይ ፡ ከፊቱ ፡ ሲሸሹ
ወዴት ፡ ልግባ ፡ ይላል ፡ ትልቁ ፡ ትንሹ

አዝ፦ እዩት ፡ ኢየሱስን ፡ መስቀሉ ፡ ማማሩ
ለተመራመረው ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ

4. ወደላይ ፡ ያረገ ፡ የከበረው ፡ ስጋው
ዳግመኛ ፡ መምጣቱ ፡ ሁላችን ፡ አንዘንጋው
በሰማይ ፡ ለሚኖር ፡ ቅዱስ ፡ አባታችን
ምሥጋና ፡ ይድረሰው ፡ ከእኛ ፡ ከሁላችን

አዝ፦ እዩት ፡ ኢየሱስን ፡ መስቀሉ ፡ ማማሩ
ለተመራመረው ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ ሚስጥሩ