From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አምላክ ፡ ሁለቱን ፡ ምራቸው
ቀድስ ፡ ኪዳናቸውን
ደስታ ፡ ሃዘን ፡ ሲቆያቸው
ዞትር ፡ ሁናቸው ፡ ተገን
ፍቅርና ፡ ቸርነት
ሰላም ፣ ደስታ ፣ አንድነት
ይደር ፡ በሚጋቡበት
በአንድነት ፡ በሚኖሩበት
ዕድሜያቸውን ፡ አርዝም
አቅልል ፡ በልጆች ፡ ደግነ
የእርጅናውን ፡ ሸክም
ይሁን ፡ ትጋት ፣ ቅንነት
የሚታገሥ ፡ በጐነት
የቤታቸው ፡ መሠረት
በዓለም ፡ በሚሄዱበት
ምራቸው ፡ በአንተ ፡ ምክር
ሊረዳዱ ፡ በትዕግሥት
ደግፋቸው ፡ በፍቅር
ፀጋን ፡ ለርሳቸው ፡ ለግሥ
ስጣቸው ፡ የአንተን ፡ ሞገሥ
ዕድሜያቸው ፡ እስኪደርስ
ብፁዕ ፡ ደሞዝን ፡ ልታድል
በፍርሃትህ ፡ ቢጸኑ
ቢያነሱት ፡ የአንተን ፡ መስቀል
ደስታህን ፡ ሊቀምሱ
በተድላ ፡ ወይ ፡ በጭንቀት
በትርፍ ፡ ሆነ ፡ በጉድለት
ይኑሩ ፡ በአንድነት
ዕድሜያቸው ፡ ሲቆለቁል
ሁለቱ ፡ ሲለያዩ
ሞት ፡ ነጥቆ ፡ አንዱን ፡ ሲነጥል
ጫ! ሲል ፡ በባዶ ፡ ቤቱ
ሃዘንተናን ፡ ደስ ፡ አሰኝ
ሁለቱን ፡ ሞት ፡ በማይገኝ
ሰብስብ ፡ በሰማይ ፡ ዕልፍኝ
|