አምላክ ፡ ሆይ ፡ የነፍሴን ፡ ጉድለት ፡ አስረዳኝ (Amlak Hoy Yenefsien Gudlet Asredagne)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አምላክ ፡ ሆይ ፡ የነፍሴን
ጉድለት ፡ አስረዳኝ
ፀጋን ፡ እንዳገኝ
ያን ፡ ጤናማ ፡ ጭንቀት
የመንፈስ ፡ ድኅነት
አትውሰድብኝ

ያለም ፡ መንገደኛ
እንደ ፡ ችጋረኛ
ራሱን ፡ በመካድ
ወደ ፡ ክርስቶስ ፡ ፀጋ
በዕምነት ፡ እንድጠጋ
ነው ፡ ያምላክ ፡ ፈቃድ

ለመዳንህ ፡ ተግተህ
በምግባር ፡ ተመክተህ
ጻድቅ ፡ ከመባል
እንዳንድ ፡ ምስኪን ፡ ርኩስ
ብትድን ፡ በኢየሱስ
ይህ ፡ ይሻልሃል

ኢየሱስ ፡ ያዳናቸው
ምስኪኖች ፡ ቀራጮች
አመሰገኑት
ፈሪሳውያን ፡ ግን
እንደ ፡ ዓለም ፡ መድኅን
አልተቀበሉትም

ጽድቅን ፡ በመፈለግ
ተስፋዬን ፡ ከማድረግ
አምላክ ፡ ያድነኝ
ነገር ፡ ግን ፡ ኦ ፡ ኢየሱስ!
ጻድቅና ፡ ቅዱስ
አንተ ፡ አድርገኝ