አምላክ ፡ እረኛዬ ፡ ነው (Amlak Eregnayie New)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

<poem>
ክንድህ ፡ ይበርታ ፡ በጠላትህ ፡ በር
ሥራቸው ፡ ይፍረስ ፡ ይድቀቅ ፡ ይሰበር ፡ ሃሌሉያ
ስምህ ፡ ይለምልም ፡ ዙፋንህ ፡ ይጽና
ለባሪያህ ፡ በጐ ፡ ውለሃልና ፡ ሃሌሉያ

አዝ፦ አምላክ ፡ እረኛዬ ፡ ነው
አምላኬ ፡ እረኛዬ ፡ ነው (፪x)

ውዳሴን ፡ ከአፌ ፡ አንተን ፡ ከልቤ
ከቶም ፡ አይጠፋ ፡ ብኖር ፡ ተርቤ ፡ ሃሌሉያ
የቅርብ ፡ ወዳጄ ፡ የጦር ፡ አዝማቼ
ተው ፡ አትለየኝ ፡ ብቆይ ፡ ታክቼ ፡ ሃሌሉያ

አዝ፦ አምላክ ፡ እረኛዬ ፡ ነው
አምላኬ ፡ እረኛዬ ፡ ነው (፪x)

ብቆም ፡ ብቀመጥ ፡ ብሄድ ፡ ብተኛ
አምላኬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ ጓደኛ ፡ ሃሌሉያ
ጽልመት ፡ ሲመጣ ፡ የመከራ ፡ ጉም
አንተን ፡ ጠርቼ ፡ እኔ ፡ አላፈርኩኝ ፡ ሃሌሉያ

አዝ፦ አምላክ ፡ እረኛዬ ፡ ነው
አምላኬ ፡ እረኛዬ ፡ ነው (፪x)

ሕመም ፡ ሞትህን ፡ ሥጋዬ ፡ ለብሶ
ይዋረድ ፡ ይለፍ ፡ ጽዋህን ፡ ቀምሶ ፡ ሃሌሉያ
የጻድቁን ፡ ሞት ፡ ነፍሴ ፡ ተጠምታ
ትጥገብ ፡ አትፈር ፡ ስምህን ፡ ጠርታ ፡ ሃሌሉያ

አዝ፦ አምላክ ፡ እረኛዬ ፡ ነው
አምላኬ ፡ እረኛዬ ፡ ነው (፪x)
</poem


ዶ/ር ለገሰ ወትሮ