አምላክ ፡ በምሕረቱ ፡ ብዛት ፡ ለሕይወት ፡ መረጠነ (Amlak Bemhiretu Bzat Lehiywot Merettene)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አምላክ ፡ በምሕረቱ ፡ ብዛት
ለሕይወት ፡ መረጠነ
በልጁም ፡ ደም ፡ ከኃጢአት
በፀጋው ፡ አጠበነ
ትምክህታችን ፡ ቀርቷል
ዕዳችንም ፡ ከብዶብናል
ፀጋን ፡ መለመን ፡ ግድ ፡ ነው

የአምላክ ፡ ትዕዛዝ ፡ ቅዱስ ፡ ነው
መታዘዝ ፡ ግን ፡ አቃተነ
ከበለእርሱ ፡ የለቀመው
ሁላችንን ፡ አሳተን
ከአዳም ፡ የሚወለድም
የአምላክን ፡ ሕግ ፡ ፈቃዱንም
ሊፈጽም ፡ አቅም ፡ አጣ

ሕግ ፡ ሁሉ ፡ እስኪፈጸም ፡ ግን
ከፍርዱ ፡ አንድንም
ጽድቅ ፡ ካላገኘን ፡ በፍርድ ፡ ቀን
አምላክ ፡ ይቅር ፡ አይለንም
ተመስገን ፡ ጌታ ፡ ልጅህን
ከዚህ ፡ ጥፋት ፡ ሊያድነን
በምሕረትህ ፡ ላክህልን

የዓለምን ፡ ሁሉ ፡ ኃጢአት
ሊሸከም ፡ የመጣልን
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ በትሩፋት
ኦሪትን ፡ ፈጸመልን
እርሱንም ፡ በተቀበለው
ያ ፡ መድኅኑ ፡ የፈጸመው
የአምላክ ፡ ሕግ ፡ አይፈርድም

የአቅማችንን ፡ ድካም
ተረድተን ፡ በመድኅን
በፈጸመልንም ፡ ሕማም
በደሙም ፡ ኃይል ፡ ስናምን
ጽድቁ ፡ ይቆጠርልናል
በአምላክም ፡ ፊት ፡ ያጸድቀናል
ልጆቹም ፡ ያደርገናል

ልጆች ፡ ከሆነ ፡ መንፈስም
ልባችንን ፡ ይገዛል
ዛፍ ፡ መልካም ፡ ከተደረገም
መልካሙን ፡ ፍሬ ፡ ያፈራል
ዕምነት ፡ ቢኖረን ፡ ፍቅርም
አይቀርም ፡ ባልንጀራውንም
ምዕመኑ ፡ ይወዳል

አምላክ ፡ እንዲህ ፡ እኛን ፡ ኃጥአን
በምሕረቱ ፡ አዳነ
ፀጋውንም ፡ ለምዕመናን
ሊሰጥ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆነ
በእኛ ፡ ጉድለት ፡ ብቻ ፡ ነው
ጽድቃችን ፡ ሁሉ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
እርሱንም ፡ እናመስግን