አምላክ ፡ በመንፈስህ ፡ የሚጋቡትን ፡ ምራቸው (Amlak Bemenfesih Yemigabutn Mirachew)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አምላክ ፡ በመንፈስህ
የሚጋቡትን ፡ ምራቸው
ወትሮ ፡ ሊኖሩልህ
አጽና ፡ አንድነታቸውን
ደስታ ፡ ሆነ ፡ ሃዘን
ሁሉ ፡ ፈቃድህን
እያመሰገኑ
ወደው ፡ ሊቀበሉ

ኦ! አምላክ ፡ ባርከው
የወንድሞችን ፡ ኪዳን
በፍቅር ፡ አሙቀው
ስጣቸው ፡ ክቡር ፡ ፀጋን
ኪዳን ፡ በሞት ፡ ሲፈርስ
አግባ ፡ በአንተ ፡ ሞገስ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ መንግሥት
የሚመኙትን ፡ ስጥ