አሜን ፡ ክበር ፡ ፀሎታችን ፡ ተሰምቷል (Amien Keber Tselotachen Tesemtual)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አሜን ፡ ክበር ፡ ፀሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅስሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፡ በፍቅር ፡ ጉዞ ፡ ጀምረናል

አሜን ፡ ጌታ ፡ ሥምህ ፡ ይባረክ
ለእኛ ፡ ለኃጢአተኞች ፡ ክንድህን ፡ ገለጽክ
ፀሎታችንን ፡ ሰምተህ ፡ አዲስ ፡ ኃይል ፡ ሰጠኸን
በጠላታችን ፡ ፊት ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አደረግኸን

አዝ፦ አሜን ፡ ክበር ፡ ፀሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅስሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፡ በፍቅር ፡ ጉዞ ፡ ጀምረናል

ጩኸታችንን ፡ ሰምቶ ፡ ጌታ ፡ ፈውሶናል
ፍቅሩን ፡ አጐናጽፎ ፡ በድል ፡ አቁሞናል
መች ፡ አየኸንና ፡ እንደ ፡ በደላችን
በትዕግሥት ፡ እያየህ ፡ ያንን ፡ ክፉ ፡ ሥራችን

አዝ፦ አሜን ፡ ክበር ፡ ፀሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅስሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፡ በፍቅር ፡ ጉዞ ፡ ጀምረናል

እኛን ፡ የገረመን ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነው
በርከክ ፡ ስንል ፡ ጭራሽ ፡ ፀሎቴን ፡ ሲሰማው
ትዕግሥተኛው ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ያስገደደው
ያዝንልናል ፡ እኮ ፡ ድካማችንን ፡ ሲያየው

አዝ፦ አሜን ፡ ክበር ፡ ፀሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅስሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፡ በፍቅር ፡ ጉዞ ፡ ጀምረናል

ጠላትም ፡ ቢከሰን ፡ ከአንተ ፡ ሊለየን
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን ፡ ቅስሙን ፡ ሰበርክልን
ይህ ፡ እኛን ፡ ሲገርመን ፡ አዲስ ፡ ኃይል ፡ ሰጠኸን
የጠላት ፡ ድል ፡ መምቻ ፡ ኃይል ፡ አጐናጸፍኸን

አዝ፦ አሜን ፡ ክበር ፡ ፀሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅስሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፡ በፍቅር ፡ ጉዞ ፡ ጀምረናል