አሜን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተባረክ (Amien Egziabhier Tebarek)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ተባረክ (፬x)

አዝ፦ አሜን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተባረክ
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የይስሐቅ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ተባረክ

1. ቅዱሳን ፡ ሁላችሁ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ባርኩ
ለሥሙ ፡ ምሥጋና ፡ እልልታን ፡ አሰሙ
እኛስ ፡ እግዚአብሔርን ፡ እንባርከዋለን
ከሲዖል ፡ መካከል ፡ ሲያወጣን ፡ ስላየን

አዝ፦ አሜን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተባረክ
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የይስሐቅ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ተባረክ

2. ኃጢአታችንን ፡ ሁሉ ፡ በልጁ ፡ ደም ፡ አጥቦ
በፊቱ ፡ አቅርቦናል ፡ አንስቶ ፡ ቀድሶ
የማንበቃውን ፡ ብቃትን ፡ ሰጥቶናል
በመንፈስ ፡ ሞልቶ ፡ ልጆች ፡ አድርጐናል

አዝ፦ አሜን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተባረክ
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የይስሐቅ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ተባረክ

3. ወደ ፡ አብ ፡ ለመግባት ፡ ድፍረት ፡ ስላገኘን
በነጻነት ፡ ሁልጊዜ ፡ በፊቱ ፡ እንቀርባለን
የጥልን ፡ ግድግዳ ፡ በስጋው ፡ አፍርሶ
በቀኙ ፡ አስቀምጦናል ፡ በክብር ፡ አንግሶ

አዝ፦ አሜን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተባረክ
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የይስሐቅ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ተባረክ

4. ያስጨናቂውን ፡ ዘንግ ፡ የሰባበርክልን
ነፍስህን ፡ በመስጠት ፡ እኛን ፡ የወደድከን
ወዳጃችን ፡ ኢየሱስ ፡ እንወድሃለን
ዘወትር ፡ ሥምህን ፡ እንባርካለን

አዝ፦ አሜን ፡ እግዚአብሔር ፡ ተባረክ
አሜን ፡ ኢየሱስ ፡ ተባረክ
የአብርሃም ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የይስሐቅ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የያዕቆብ ፡ አምላክ ፡ ተባረክ
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ ተባረክ