From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
1. ባህር ፡ ተናወጠች ፡ ተራሮችም ፡ ጨሱ
የሰማያት ፡ አምላክ ፡ ወጣ ፡ ከመቅደሱ
ክብሩ ፡ ምድርን ፡ ሞላ ፡ ቁጣውም ፡ ነደደ
ለልጆቹ ፡ ሊያግዝ ፡ ጌታችን ፡ ወረደ
አዝ፦ አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
ለዚህ ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ ለረዳን
ውርደትን ፡ በክብር ፡ ለውጦ
ጠላታችንንም ፡ ቀጥቅጦ
እኛን ፡ ላበዛን
2. እግዚአብሔር ፡ ነገሠ ፡ አሕዛብ ፡ ደነገጡ
በኪሩቤል ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ በመቀመጡ
እነዚያ ፡ በፈረስ ፡ በሠረገላቸው
ቢታመኑበትም ፡ ጌታ ፡ አሳፈራቸው
አዝ፦ አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
ለዚህ ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ ለረዳን
ውርደትን ፡ በክብር ፡ ለውጦ
ጠላታችንንም ፡ ቀጥቅጦ
እኛን ፡ ላበዛን
3. ድምጹ ፡ አንዴ ፡ ነጐድጓድ ፡ ክብርን ፡ የለበሰ
መልኩ ፡ ሰባት ፡ ጊዜ ፡ ከፀሐይ ፡ የባሰ
ፈነጠቀባቸው ፡ የብርሃኑን ፡ ጮራ
እንዳለ ፡ ሊያስታውቅ ፡ ከልጆቹ ፡ ጋራ
አዝ፦ አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
ለዚህ ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ ለረዳን
ውርደትን ፡ በክብር ፡ ለውጦ
ጠላታችንንም ፡ ቀጥቅጦ
እኛን ፡ ላበዛን
4 ምድርና ፡ ሞላዋ ፡ አላምላካችን ፡ ናት
ዓለምና ፡ በእርሷ ፡ ሁሉ ፡ የሚኖሩት
እግዚአብሔር ፡ ወረደ ፡ በተራሮች ፡ መሃል
በክብር ፡ ተሞልቶ ፡ እኛን ፡ ለመከለል
አዝ፦ አሜን ፡ በሉ ፡ ስገዱለት
ለዚህ ፡ አምላክ ፡ እኛን ፡ ለረዳን
ውርደትን ፡ በክብር ፡ ለውጦ
ጠላታችንንም ፡ ቀጥቅጦ
እኛን ፡ ላበዛን
|