አመስግኑት ፡ ክርስቶስን ፡ መድኃኒታችን (Amesgenut Kristosen Medhanitachen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አመስግኑት ፡ ክርስቶስ ፡ መድኃኒታችን
ዘምሩ ፣ ፍቅሩንም ፡ አስታውቁ
አመስግኑት ፡ ክርስቶስን ፡ የጥንት ፡ አምባችን
ክብርም ፣ ሁሉ ፡ ይሁንለት ፡ ለርሱ
ኢየሱስ ፡ ነውና ፣ ቸሩ ፡ ጠባቂያችን
በክንዱም ፣ ይሸከመናል ፡ እርሱ
አመስግኑት ፣ ታላቅ ፡ ነው ፡ መድኃኒታችን
አመስግኑት ፣ የሱስን ፡ አክብሩ!

አመስግኑት ፣ ክርስቶስን ፡ መድኃኒታችን
ለእኛ ፡ ሲል ፣ ደሙን ፡ አፈሰሰ
አምላካችን ፡ ነው ፣ ተስፋችን ፡ መጠጊያችን
ይንገሥ ፣ ይንገሥ ፣ ሞትን ፡ ያሸነፈ!
ስገዱለት ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ንጉሣችን
ታላቅ ፡ ፍቅሩን ፡ ለእኛ ፡ የገለጠ
አመስግኑት ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ መድኃኒታችን
ክብር ፡ ይሁን ፣ ከሞት ፡ ላዳነነ!

አመስግኑት ፡ ክርስቶስን ፡ መድኃኒታችን
አዲስ ፡ ቅዱስ ፡ ቅኔ ፡ ተቀኙለት
ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ይንገሥልን ፡ በልባችን
ይንገሥ ፣ ይንገሥ ፣ ለርሱ ፡ ይሁን ፡ ስብሐት
ሊመጣ ፡ ነው ፡ ነቢይ ፡ ሊቀ ፡ ካሕናችን
ክብር ፣ ኃይልም ፡ ለርሱ ፡ ሊሆንለት
አመስግኑት ፡ ታላቅ ፡ ነው ፡ መድኃኒታችን
አመስግኑ ፣ የሱስን ፡ አክብሩ!