From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ ፣
አሜን ፣ ክበር ፣
ጸሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅሥሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፣ በፍቅር ፣
ጉዞ ፡ ጀምረናል ።
አሜን ፣ ክበር ፣ ጌታ ፡ ስምህ ፡ ይባረክ
ለእኛ ፡ ኃጢአተኞች ፡ ኃይልህን ፡ ገለጽክ
ጸሎታችንን ፡ ሰማህ ፣ አዲስ ፡ ኃይል ፡ ሰጠኸን
በጠላታችን ፡ ፊት ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ አደረግኸን
አዝ ፣
አሜን ፣ ክበር ፣
ጸሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅሥሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፣ በፍቅር ፣
ጉዞ ፡ ጀምረናል ።
ጩኸታችንን ፡ ሰምቷል ፣ ጌታ ፡ ፈውሶናል
ፍቅሩን ፡ አጐናጽፎ ፡ በድል ፡ አቁሞናል
መች ፡ አየኸንና ፡ እንደ ፡ በደላችን
በትዕግሥት ፡ እያየህ ፡ ያን ፡ ክፉ ፡ ሥራችን
አዝ ፣
አሜን ፣ ክበር ፣
ጸሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅሥሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፣ በፍቅር ፣
ጉዞ ፡ ጀምረናል ።
እኛን ፡ የገረመን ፡ የጌታ ፡ ፍቅር ፡ ነው
በርከክ ፡ ስንል ፡ ጭራሽ ፡ ፀሎትን ፡ ሲሰማው
ትዕግሥተኛው ፡ ጌታ ፡ ፍቅር ፡ ያስገደደው
ያዝንልናል ፡ እኮ ፡ ድካማችን ፡ ሲያየው
አዝ ፣
አሜን ፣ ክበር ፣
ጸሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅሥሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፣ በፍቅር ፣
ጉዞ ፡ ጀምረናል ።
ጠላትም ፡ ቢከሰን ፡ ከአንተ ፡ ሊለየን
እግዚአብሔር ፡ ተመስገን ፣ ቅስሙን ፡ ሰበርክልን
ይህ ፡ እኛን ፡ ሲገርመን ፡ አዲስ ፡ ኃይል ፡ ሰጠኸን
የጠላት ፡ ድል ፡ መምቻ ፡ ኃይል ፡ አጐናጸፍኸን ።
አዝ ፣
አሜን ፣ ክበር ፣
ጸሎታችን ፡ ተሰምቷል
ጠላት ፡ ቅሥሙ ፡ ተሰብሯል
በአዲስ ፡ ኃይል ፣ በፍቅር ፣
ጉዞ ፡ ጀምረናል ።
|