አምባችን ፡ አምላካችን (Ambachen Amlakachen New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አምባችን ፡ አምላካችን ፡ ነው
ብርቱ ፡ እቃ ፡ ጦራችን
በመከራችን ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ ጽኑ ፡ መጠጊያችን
የጥንት ፡ ጠላታችን ፡ ሊያጠፋን ፡ ሲሻ
በኃይል ፡ በተንኮል ፡ ቃል ፡ ጥላቻንም ፡ ለብሶ
የሰው ፡ ኃይል ፡ አይችለውም

በኃይላችን ፡ ብንታመን ፡ ቶሎ ፡ እንጠፋለን
ግን ፡ እግዚአብሔር ፡ የመረጠው
እርሱ ፡ በእኛ ፡በኩል ፡ ነው
ሥሙንም ፡ ብትጠይቅ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር
ፀባኦት ፡ የማይለወጠው
እርሱ ፡ ነው ፡ ድል ፡ አድራጊው

ዓለም ፡ በሰይጣን ፡ ቢሞላም ፡ በጣም ፡ ቢያስፈራራንም
እውነት ፡ እንደምታሸንፍ ፡ አምላክ ፡ ፈቃዱ ፡ ሆኗል
ዘመድ ፡ ገንዘብ ፡ ይቅር ፡ ሟቹ ፡ ሕይወት ፡ ጭምር
ገላን ፡ የሚገድሉ ፡ እውነትህን ፡ አይገድሉም
መንግሥትህ ፡ ነዋሪ ፡ ነው