አማኑኤል (Amanuel)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አማኑኤል ፡ አሜን ፡ አሜን (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው

1. አብ ፡ ልጁን ፡ ላከልን ፡ ክብሩንም ፡ አየን
በሞት ፡ ጥላ ፡ ሳለን ፡ ብርሃን ፡ ወጣልን

አዝ፦ አማኑኤል ፡ አሜን ፡ አሜን (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው

2. ከሰማይ ፡ ወረደ ፡ ከድንግል ፡ ተወለደ
ከሙታን ፡ ተነሣ ፡ ሁሉንም ፡ ድል ፡ ነሣ

አዝ፦ አማኑኤል ፡ አሜን ፡ አሜን (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው

3. የበጉን ፡ ቃል ፡ ስሙ ፡ በእምነት ፡ ተቀበሉ
የመንፈስ ፡ ቅዱስን ፡ ክብር ፡ እንድትወርሱ

አዝ፦ አማኑኤል ፡ አሜን ፡ አሜን (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው

4. በአባቱ ፡ ቀኝ ፡ ያለው ፡ በመንፈስ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው
በቃል ፡ ይሟገታል ፡ ድሉን ፡ ያሳየናል

አዝ፦ አማኑኤል ፡ አሜን ፡ አሜን (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ነው