አምላክን ፡ አክብሩ (Amlakn Akbru)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አምላክን ፡ አክብሩ
ዕሙን ፡ ነው ፡ ምክሩ
ይስፋ ፡ ክብሩ
በኃይሉ ፡ ነግሦአል
ፀጋን ፡ ለግሶልናል
እንዴት ፡ ያስደንቃል?
ታላቅ ፡ ፍቅሩ

ተዋረደ ፡ ለሰው
ጽዋውም ፡ መረረው
ሲቀበለው
መድኃኒቱም ፡ ሲሞት
መላዕክት ፡ አደነቁት
መሰቀሉም ፡ ሕይወት
ሊሰጠን ፡ ነው

ምሕረቱ ፡ ታላቅ ፡ ነው
ሊያመሰግነው
አይበቃም ፡ ሰው
አንድ ፡ ቀን ፡ ግን ፡ በሰማይ
ግርማውን ፡ በግልጥ ፡ ስናይ
ምሥጋናው ፡ የቀላይ
ምሣሌ ፡ ነው

ግን ፡ በዚህ ፡ ታች ፡ አሁን
ጀምሩ ፡ አዲሱን
ድንቅ ፡ መዝሙሩን
የአምላክ ፡ ነው ፡ መንግሥትም
ኃይል ፡ ገናንነትም
እስከ ፡ ዘለዓለምም
ለእርሱ ፡ ይሁን