አልረሳውም ፡ ያንን ፡ ጊዜ (Alresawum Yanin Gizie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አልረሳውም ፡ ያንን ፡ ጊዜ ፡ በጌቴሴማኒ
በጣርህ ፡ ደም ፡ ሲያልብህ
ስለእኔ ፡ አምላኬ!
አልረሳውም ፡ አልረሳውም
ከቶ ፡ አልረሳውም
የብርቱ ፡ ጣርህን ፡ ጊዜ
በጌቴሴማኒ

በዚያ ፡ ሥፍራ ፣ ባታክልቱ
በልቤ ፡ አየሁህ
ቤዛ ፡ ሆነህ ፡ የፍርድ ፡ መዓት
እንደ ፡ ተቀበልህ
አልረሳውም ፣ አልረሳውም
ከቶ ፡ አልረሳውም
የብርቱ ፡ ጣርህን ፡ ጊዜ
በጌቴሴማኒ

ወዳጆችህ ፣ ሁሉ ፡ ካዱህ
አልራራልህም ፡ ዓብ
ያ ፡ ብርቱ ፡ ችግርህ ፡ ጊዜ
አይመዘንም ፡ በሃሣብ
አልረሳውም ፣ አልረሳውም
ከቶ ፡ አልረሳውም
የብርቱ ፡ ጣርህን ፡ ጊዜ
በጌቴሴማኒ

ፍቅሬ ፡ ቢበርድብኝ ፡ ለአንተ
ክቡር ፡ መድኃኒቴ
ሕማማትህን ፡ አሳስበኝ
አሳየኝ ፡ ቁስልህን
እንዳልረሳው ፣ እንዳልረሳው
ይህን ፣ እንዳልረሳው
የብርቱ ፡ ጣርህን ፡ ጊዜ
በጌቴሴማኒ

ስለእኔ ፡ ነው ፣ ስለእኔ ፡ ነው
ደምህ ፡ የፈሰሰው
እንዳመሰግንህ ፡ ጌታ
ክፈትልኝ ፡ አፌን
እንዳልረሳው ፣ እንዳልረሳው
ይህን ፣ እንዳልረሳው
የብርቱ ፡ ጣርህን ፡ ጊዜ
በጌቴሴማኒ