አለት ፡ ቢፈርሥም ፡ ተራራ ፡ ቢወድቅም (Alet Bifersm Terara Biwodqm)
From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አለት ፡ ቢፈርሥም ፡ ተራራ ፡ ቢወድቅም
ዕምነቴ ፡ እስከ ፡ ዘለዓለሙ ፡ ነው
የኪዳኔም ፡ ፀጋ ፡ ከአንቺ ፡ አይርቅም
እንዲህ ፡ የሚልሽ ፡ መድኃኒትሽ ፡ ነው
ኦ ! ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ያን ፡ ቃል ፡ እንዳልረሳ
ተስፋህንም ፡ እንድታመን ፡ እርዳኝ
ከመቃብሬም ፡ ከእንቅልፌም ፡ ስነሣ
ያ ፡ ክቡር ፡ ቃልህ ፡ በቤትህ ፡ ያግባኝ
|