አልጨነቅም ፡ ለመከራ (Alecheneqem Lemekera)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ አልጨነቅም ፡ ለመከራ
አምላክ ፡ ካለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

በሰጠኝ ፡ ተስፋ ፡ እጸናለሁ
በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ አምኛለሁ
ከብስጭት ፡ እንድትድኑ
ሁላችሁም ፡ በእርሱ ፡ እመኑ (፪x)

አዝ፦ አልጨነቅም ፡ ለመከራ
አምላክ ፡ ካለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

አትጨነቁ ፡ ለዚህ ፡ ዓለም
ከኢየሱስ ፡ የሚበልጥ ፡ የለም
እናቶቼ ፡ አባቶቼ
አትታለሉ ፡ ዘመዶቼ
እህቶቼ ፡ ወንድሞቼ
አትዘንጉ ፡ ወገኖቼ

አዝ፦ አልጨነቅም ፡ ለመከራ
አምላክ ፡ ካለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ዓለም ፡ ያልፋል ፡ ሀብትም ፡ ሁሉ
የሚወዱን ፡ ይለያሉ
ሞት ፡ ሲመጣ ፡ ጣር ፡ ሲከበን
ያኔ ፡ የለም ፡ የሚያድነን

አዝ፦ አልጨነቅም ፡ ለመከራ
አምላክ ፡ ካለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ያታለሉን ፡ ነገሮች ፡ ሁሉ
ከፊታችን ፡ ይሸሻሉ
የማይለይ ፡ የማይጠፋ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ቋሚ ፡ ተስፋ

አዝ፦ አልጨነቅም ፡ ለመከራ
አምላክ ፡ ካለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)

ሁላችሁም ፡ ብልኅ ፡ ሁኑ
በኢየሱስ ፡ አሁን ፡ እመኑ
ተናዘዙ ፡ ለፈጣሪ
ርኅሩኅ ፡ ነው ፡ ቸር ፡ መሐሪ (፪x)

አዝ፦ አልጨነቅም ፡ ለመከራ
አምላክ ፡ ካለ ፡ ከእኔ ፡ ጋራ (፪x)