አንድ ፡ ቀን ፡ በአምላክ ፡ አዳራሽ (Aind Qen BeAmlak Adarash)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አንድ ፡ ቀን ፡ በአምላክ ፡ አዳራሽ
ከምድር ፡ ወገን ፡ ሁሉ
ሊቆጠሩ ፡ የማይቻሉ
ፃድቃን ፡ ይቆማሉ

አንድ ፡ ቀን ፡ የአምላክ ፡ አገልጋዮች
በመከሩ ፡ ወራት
ያያሉ ፡ ከተማሩቱ
የእልፍ ፡ አዕላፋት

ሲሰጠን ፡ በሰማይ ፡ ፀዳል
ሰላምም ፣ ብፅዕናም
ምንኛ ፡ ደስታ ፡ ይሆናል?
ምንኛ ፡ ምሥጋናም

ኦ! አምላክ ፡ ፀጋህ ፡ ትልቅ ፡ ነው
ወደ ፡ አንተ ፡ አቅርበን
ከፃድቃን ፡ ጋር ፡ እንድንገኝ
በዚያ ፡ ታላቅ ፡ ቀን