አሁን ፡ መሽቶአልና (Ahun Meshtoalina)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አሁን ፡ መሽቶአልና
ቅረበኝ ፡ ኦ! ኢየሱስ
በኪዳንህ ፡ ልጽና
ፍቅርህን ፡ አስታውስ
ደግስልኝ ፡ ፀጋህን
ግለጽልኝ ፡ ወንጌልን
ክብረትህ ፡ በሚገለጥ
ለሚያምኑበት

ኢየሱስ ፡ ልቤን ፡ አሁን ፡ ሳብ
ወደ ፡ ቅዱስ ፡ ቃልህ
አግባልኝ ፡ ቅዱስ ፡ ሃሣብ
አጥራኝ ፡ በደምህ
ለመከተል ፡ ደግፈኝ
ለመታገል ፡ ኃይል ፡ ስጠኝ
ከሰማያዊ ፡ መዝገብ
ለእኔ ፡ አገናዝብ

በዚህ ፡ ዛሬ ፡ የቆየኝ
ሃዘን ፡ ሆኖ ፡ ተድላ
ልቤን ፡ ደስ ፡ የሚያሰኝ
ወይም ፡ ማበሳጫ
ሁልን ፡ ላንት ፡ ላስታውቅ ፡ ነኝ
ልመናዬን ፡ ስማልኝ
ለግስልኝ ፡ በየውሃት
እንደ ፡ ርኅሩኅ ፡ አባት

ድሃ ፡ ምስኪንም ፡ ሾን
ሁሉ ፡ ቀን ፡ ልወድስ
ለክብረትህ ፡ እንዲሆን
አንተ ፡ አፌን ፡ ቀድስ
እስካሁን ፡ ነህ ፡ ተስፋዬ
የዳንሁበት ፡ ጋሻዬ
እስካሁን ፡ የደገፍኸኝ
ዞትር ፡ ልትረዳኝ