አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞልቶታል (Afien Saq Moltotal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዐይኔ ፡ መልካም ፡ ነገር ፡ ከእንግዲህ ፡ አያይም
ተስፋ ፡ የሚሆነኝ ፡ ፍፁም ፡ አላገኝም
እያለ ፡ በምሬት ፡ ለተሞላው ፡ ልቤ
ርቋል ፡ ያልኩት ፡ ጌታ ፡ መጥቶ ፡ አጠገቤ
ቃሌን ፡ አዳመጠ ፡ መልሴን ፡ መለሰልኝ
ምሬትን ፡ አጥፍቶ ፡ በደስታ ፡ አዘለለኝ (፪x)

አዝ፦ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞልቶታል ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ደስታዬን ፡ ልቆጥብ ፡ እንዴት ፡ እችላለሁ
ማዳኑን ፡ እያየሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገውን
እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ጌታዬ ፡ ባርኮኛል ፡ እዘምራለሁኝ
ኢየሱስ ፡ ደስ ፡ ይበለው ፡ እዘምራለሁኝ

ልቤን ፡ ሃዘን ፡ ከቦት ፡ ትካዜዬ ፡ በዝቶ
አለኝ ፡ ያልኩት ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ከእኔ ፡ ጠፍቶ
በቁስል ፡ ላይ ፡ ቁስል ፡ ወጥቶብኝ ፡ እያለ
ኢየሱስ ፡ እኔን ፡ ሊያክም ፡ ፈጥኖ ፡ ከተፍ ፡ አለ
ሥጋዬም ፡ ታደሰ ፡ ልምላሜ ፡ አገኘሁ
ተርፌአለሁ ፡ ከሞት ፡ ይኸው ፡ በሕይወት ፡ አለሁ (፪x)

አዝ፦ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞልቶታል ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ደስታዬን ፡ ልቆጥብ ፡ እንዴት ፡ እችላለሁ
ማዳኑን ፡ እያየሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገውን
እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ጌታዬ ፡ ባርኮኛል ፡ እዘምራለሁኝ
ኢየሱስ ፡ ደስ ፡ ይበለው ፡ እዘምራለሁኝ

መሳለቂያ ፡ ሆኜ ፡ ለባልንጀሮቼ
ያለኝ ፡ ክብር ፡ ጠፍቶ ፡ ከሰው ፡ ተለይቼ
ቀኑ ፡ ጨልሞብኝ ፡ ግራ ፡ ተጋብቼ
ኢየሱስ ፡ ሲመጣ ፡ አየሁት ፡ በዐይኖቼ
እያዩኝ ፡ ባይናቸው ፡ የናቁኝ ፡ በሙሉ
ጌታዬ ፡ አከበረኝ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ
ኢየሱስ ፡ አከበረኝ ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ ለእርሱ (፪x)

አዝ፦ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞልቶታል ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ደስታዬን ፡ ልቆጥብ ፡ እንዴት ፡ እችላለሁ
ማዳኑን ፡ እያየሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገውን
እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ጌታዬ ፡ ባርኮኛል ፡ እዘምራለሁኝ
ኢየሱስ ፡ ደስ ፡ ይበለው ፡ እዘምራለሁኝ

ሞቴን ፡ ስትጠብቁ ፡ ህመሜን ፡ አይታችሁ
እግዚአብሔር ፡ ትቶታል ፡ ረስቶታል ፡ ያላችሁ
እኔ ፡ ግን ፡ አልሞትሁም ፡ በሕይወት ፡ አለሁኝ
እንዲያውም ፡ አምሮብኝ ፡ ለምልሜ ፡ አለሁ ፡ እዩኝ
ምርኮዬን ፡ መልሷል ፡ እጥፍ ፡ ድርብ ፡ አርጐ
ከፊተኛው ፡ ይልቅ ፡ የአሁኑን ፡ አብልጦ (፪x)

አዝ፦ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞልቶታል ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ደስታዬን ፡ ልቆጥብ ፡ እንዴት ፡ እችላለሁ
ማዳኑን ፡ እያየሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገውን
እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ጌታዬ ፡ ባርኮኛል ፡ እዘምራለሁኝ
ኢየሱስ ፡ ደስ ፡ ይበለው ፡ እዘምራለሁኝ

እንዳለፈ ፡ ውኃ መከራዬን ፡ ረሳሁ
የቀድሞ ፡ ዘመኔን ፡ ደጋግሜ ፡ ላላየው
ለማውም ፡ ሁሉ ፡ ብርሃን ፡ ሆኖልኛል
እፎይ ፡ ብያለሁኝ ፡ ጌታ ፡ አሳርፎኛል
እፎይ ፡ በርትቻለሁ ፡ ሕይወቴም ፡ ያበራል
ኑሮዬ ፡ በሙሉ ፡ በኢየሱስ ፡ ጣፍጧል (፪x)

አዝ፦ አፌን ፡ ሳቅ ፡ ሞልቶታል ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ እላለሁ
ደስታዬን ፡ ልቆጥብ ፡ እንዴት ፡ እችላለሁ
ማዳኑን ፡ እያየሁ ፡ ለእኔ ፡ ያደረገውን
እንዳልተቀበለ ፡ እንዴት ፡ እሆናለሁ
ጌታዬ ፡ ባርኮኛል ፡ እዘምራለሁኝ
ኢየሱስ ፡ ደስ ፡ ይበለው ፡ እዘምራለሁኝ