አፌን ፡ ምሥጋና ፡ ሞላው (Afien Mesgana Molaw)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝአፌን ፡ ምሥጋና ፡ ሞላው ፡ ሆ...ሆ (፪x)
በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
ሞትን ፡ እርግጬ ፡ ይኸው ፡ ዘምራለሁ ፡ አሸበሽባለሁ

ነፍሴንም ፡ ፈለጓት ፡ በአንድነት ፡ ተማርከው
እግዚአብሔር ፡ ትቶታል ፡ አይረዳውም ፡ ብለው
ጉድጓድ ፡ የማሱልኝ ፡ ጽዋቸውን ፡ ያነሱ
በትንሳኤው ፡ ስልጣን ፡ ሃፍረትን ፡ ለበሱ

አዝአፌን ፡ ምሥጋና ፡ ሞላው ፡ ሆ...ሆ (፪x)
በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
ሞትን ፡ እርግጬ ፡ ይኸው ፡ ዘምራለሁ ፡ አሸበሽባለሁ

ሞት ፡ ጥላ ፡ አጥልቶብኝ ፡ ክንዱን ፡ እያሳየኝ
በእኔ ፡ ሊሰለጥን ፡ አሳቢ ፡ እንደሌለኝ
መቃብር ፡ ፈንቅሎ ፡ ከሞት ፡ የተነሳው
ኢየሱስ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ መውጊያውን ፡ ሰበረው

አዝአፌን ፡ ምሥጋና ፡ ሞላው ፡ ሆ...ሆ (፪x)
በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
ሞትን ፡ እርግጬ ፡ ይኸው ፡ ዘምራለሁ ፡ አሸበሽባለሁ

ነፊሴን ፡ ያሸበራት ፡ የዲያቢሎስ ፡ መንጋ
ቅስሙ ፡ ተሰባብሮ ፡ ወዶ ፡ ጥልቁ ፡ ገባ
የሟርተኞችን ፡ አፍ ፡ የክፉን ፡ አንደበት
ዘጋልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ በትንሳኤው ፡ ጉልበት

አዝአፌን ፡ ምሥጋና ፡ ሞላው ፡ ሆ...ሆ (፪x)
በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
ሞትን ፡ እርግጬ ፡ ይኸው ፡ ዘምራለሁ ፡ አሸበሽባለሁ

ሁልጊዜ ፡ ስራውን ፡ ጽድቁን ፡ አስባለሁ
የማዳኑን ፡ ስራ ፡ ለሰዎች ፡ እነግራለሁ
የሚያዩኝ ፡ ይደነቁ ፡ ደስ ፡ አሰኝቶኛል
በልቤም ፡ በአፌም ፡ ምሥጋናውን ፡ ሞልቶታል

አዝአፌን ፡ ምሥጋና ፡ ሞላው ፡ ሆ...ሆ (፪x)
በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
ሞትን ፡ እርግጬ ፡ ይኸው ፡ ዘምራለሁ ፡ አሸበሽባለሁ

ያንሰዋል ፡ ዝማሬ ፡ ያንሰዋል ፡ ዕልልታ
ምን ፡ ቃል ፡ ይገልጸዋል ፡ የጌታን ፡ ውለታ
እንዲያው ፡ ላወድሰው ፡ ላሸበሽብ ፡ ለስሙ
በምድር ፡ በአርያም ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ ዙፋኑ

አዝአፌን ፡ ምሥጋና ፡ ሞላው ፡ ሆ...ሆ (፪x)
በኢየሱስ ፡ ትንሳኤ ፡ ሕይወት ፡ አግኝቻለሁ
ሞትን ፡ እርግጬ ፡ ይኸው ፡ ዘምራለሁ ፡ አሸበሽባለሁ