አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ እንዘምር (Addis Zemarie Enzemer)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በእረኛቸው ፡ የታመኑ ፡ በየመስኩ ፡ የተሰማሩ
ዱካውን ፡ እየተከተሉ ፡ ለደህንነት ፡ የተጠሩ
ከጨካኝ ፡ አውሬ ፡ የዳኑ ፡ ከመታረድ ፡ የተረፉ
ሃሴትን ፡ እንደሚያደርጉ ፡ በአጥፊው ፡ ጥፋት ፡ ስላልጠፋ

አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ እንዘምር
ለመድሃኒታችን ፡ ክብር
የምሥጋናችንን ፡ ሽታ
እናሳርግ ፡ በዕልልታ

ማቃችንን ፡ ቀዷልና ፡ ፀጋውን ፡ አልብሶናልና
ክብራችን ፡ ትዘምርለት ፡ ፍቅሩ ፡ አጽናንቶናልና
ጉዳታችንን ፡ የሚሹ ፡ ጉድጓድ ፡ ምሰው ፡ የጠበቁን
አጋንንት ፡ አፍረዋልና ፡ ያደፈጡ ፡ ሊያጠቁን

አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ እንዘምር
ለመድሃኒታችን ፡ ክብር
የምሥጋናችንን ፡ ሽታ
እናሳርግ ፡ በዕልልታ

በፍፁም ፡ ልብ ፡ እንዘምር ፡ በአምላካችን ፡ ደስ ፡ ይበለን
እናጨበጭብ ፡ እልል ፡ እንበል ፡ ለምንስ ፡ እንቆጥባለን
በምሥጋናችን ፡ ዝማሬ ፡ ምሽጉን ፡ እናፈርሳለን
በመንፈሳዊ ፡ ጦር ፡ እቃ ፡ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን

አዝ፦ አዲስ ፡ ዝማሬ ፡ እንዘምር
ለመድሃኒታችን ፡ ክብር
የምሥጋናችንን ፡ ሽታ
እናሳርግ ፡ በዕልልታ