From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዲስ ፡ ያልተወለደ ፡ ለአዲስ ፡ ሕይወት
የአምላክን ፡ መንግሥት ፡ አያይም
ክርስቶስን ፡ ያልያዘ ፡ በልብ ፡ ኃይማኖት
ወደ ፡ ሰማይም ፡ አይገባም
ደጁም ፡ ጠባብ ፡ ነው ፣ ተጋደል ፡ ለመግባት
ቀንም ፡ አጭር ፡ ነች ፣ እንዳታባክናት
ልትጥር ፡ ያስፈልግሃል ፡ በፍርሃት
እንዳይቀርብህ ፡ ብፅዕናው
ሰምተህ ፡ ከመዳን ፡ ይከለክልሃል
ሰይጣን ፣ ያ ፡ ክፉ ፡ ጠላትህ
በዓለም ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ያታልልሃል
እንዳትድን ፡ ከጥፋትህ
ድምጹን ፡ አትስማ ፣ ፍራው ፡ ወዳጄ ፡ ሆይ!
ከዓለም ፡ ምንጮች ፡ ራቅ ፣ በዚያም ፡ አትቆይ
ንስሐ ፡ ለማድረግም ፡ አትዘግይ
ኢየሱስ ፡ በፍቅር ፡ ሲጠራህ
በሰማይ ፡ ለፃርህ ፡ ለትግልህም
ምን ፡ ያህል ፡ ወረታ ፡ አለህ?
ወዲያም ፡ ከደረስህ ፡ አይጸጽትህም
አክሊልህን ፡ ታገኛለህ
ስለዚህ ፡ ተነሥ ፣ አሁንም ፡ ተዘጋጅ
ይቀርብብሃል ፡ የዓለሙ ፡ ፈራጅ
የሠርግ ፡ ልብስ ፡ ያለበሰው ፡ በሰማይ ፡ ደጅ
እስከ ፡ ዘለዓለም ፡ አይገባም
ዕውነተኛ ፡ ዕምነት ፡ በልብህ ፡ ባይገኝ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ አትደርስም
የክርስቶስን ፡ ጽድቅ ፡ ልትለብስ ፡ ባትመኝ
ሕይወትንም ፡ አትወርስም
ልትድን ፡ ከሆንህ ፡ በዕምነት ፡ ብቻ ፡ ነው
የክርስቶስን ፡ ጽድቅ ፡ አሁን ፡ ተቀበለው
ኢየሱስም ፡ በፍቅር ፡ ሲጠራህ ፡ ስማው
እርሱን ፡ የሰማ ፡ ይድናል
የሕይወትን ፡ ዘውድ ፡ እንዲጭን ፡ ለመጣር
ዓለሙ ፡ ሁሉ ፡ ተጠራ
ለአንተም ፡ ዘውድ ፡ ተዋጀ ፡ በኢየሱስ ፡ ተግባር
ለአንተም ፡ በፍቅሩ ፡ ራራ
ታላቁ ፡ መሐሪ ፡ ያዝንልሃል
እጁንም ፡ በፍቅር ፡ ዘርግቶልሃል
ከእንቅልፍህም ፡ ይቀሰቅስሃል
ብፁዕ ፡ ነህ ፡ ብትነቃለት
|