አዳም ፡ በውድቀቱ ፡ ያወረደብን ፡ ሁሉ (Adam Bewudqetu Yaweredeben Hulu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዳም ፡ በውድቀቱ ፡ ያወረደብን ፡ ሁሉ
በሴት ፡ ዘር ፡ ተፈውሶዋል
ክርስቶስ ፡ በመስቀሉም ፡ ላይ ፡ ሲሞትልን
ኃጢአታችንን ፡ አርቆዋል
በእንጨት ፡ ላይ ፡ የሞት ፡ ሥቃይ
ቅዱሱ ፡ ስለ ፡ ኃጢኣን ፡ ቀምሶዋል

ደሜን ፡ ሥጋዬንም ፡ እንኩ ፡ ውሰዱ
ይህ ፡ ነው ፡ የኃጢአታችሁ ፡ ሥርየት
አለና ፡ ወደ ፡ ሕማም ፡ በመሄዱ
አወረደልን ፡ የዓብን ፡ ሥምረት
ግሩም ፡ ጭንቁንም ፡ መስቀሉንም
ተሸክሞልን ፡ ዋጀልን ፡ ሥርየት

አበሣህም ፡ እንደ ፡ ቅርምዝ ፡ ቢሆንም
በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ ማጥራት ፡ ይችላል
ኢየሱስ ፡ በመስቀል ፡ ከሞተ ፡ መዳንም
ጽድቅም ፡ ብጽዕናም ፡ ተሰጥቶናል
የእርሱን ፡ ሥቃይ ፡ በዕምነት ፡ ብታይ
ከሞት ፡ ከመቅሠፍትም ፡ ያድንሃል

ግን ፡ የመድኃኒቱን ፡ ደም ፡ የሚንቁ
ፍርድን ፡ ሳይፈሩ ፡ የፀጋን ፡ ብዛት
ችላ ፡ እያሉ ፡ ከኢየሱስ ፡ ሲርቁ
ምን ፡ ያድናቸው ፡ ይሆን ፡ ከጥፋት?
የናቁትን ፡ ቸር ፡ መድኅን
ግርማውን ፡ ሲለብስ ፡ ያዩታል
በፍርሃት!

ኦ! ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በቅዱስ ፡ ሕማምህ
ኃጢአተኞችን ፡ አድነሃል
ለመንፈሣችን ፡ ዕረፍት ፡ በድካምህ
እንድትሰጠን ፡ ተጨንቀሃል
ሁላችንን ፡ ልታድነን
በቅዱስ ፡ መስቀልህ ፡ ገዝተኸናል

አንተ ፡ በጐልጐታ ፡ ላይ ፡ የሞትህልን
ኦ! ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ለማመን ፡ እርዳን
የሠራህልንንም ፡ ግለጥልን
እኛም ፡ በመስቀልህ ፡ ኃይል ፡ እንዳን
መስቀልህም ፡ ለዘለዓለም
ተስፋን ፡ ሕይወት ፡ ሊሰጠን ፡ ያብቃን