አዳም ፡ በውድቀቱ ፡ ያወረደብን (Adam Bewdqetu Yaweredebn)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዳም ፡ በውድቀቱ ፡ ያወረደብን
ሁሉ ፡ በሴት ፡ ዘር ፡ ተፈውሷል
ክርስቶስ ፡ በመስቀሉም ፡ ላይ ፡ ሲሞትልን
ኃጢአታችንን ፡ አርቋል
በእንጨት ፡ ላይ
የሞት ፡ ሥቃይ
ቅዱሱ ፡ ስለ ፡ ኃጥአን ፡ ቀምሷል

ደሜን ፡ ሥጋዬንም ፡ እንኩ ፡ ውሰዱ
ይህ ፡ ነው ፡ የኃጢአታችሁ ፡ ሥርየት
አለና ፡ ወደ ፡ ሕማም ፡ በመሄዱ
አወረደልን ፡ የዓብን ፡ ሥምረት
ግሩም ፡ ጭንቁንም
መስቀሉንም ፡ ተሸክሞልን
ዋጀልን ፡ ሥርየት

አበሣህም ፡ እንደ ፡ ቅርምዝ ፡ ቢሆንም
በቅዱስ ፡ ደሙ ፡ መጥራት ፡ ይችላል
ኢየሱስ ፡ በመስቀሉ ፡ ከሞተ
መዳንም ፣ ጽድቅም ፣ ብጽዕናን ፡ ተሰጥቶናል
የእርሱን ፡ ሥቃይ
በዕምነት ፡ ብታይ
ከሞት ፡ ከመቅሠፍትም ፡ ያድንሃል

ግን ፡ የመድኃኒቱን ፡ ደም ፡ የሚንቁ
ፍርድን ፡ ሳይፈሩ ፡ የፀጋን ፡ ብዛት
ችላ ፡ እያሉ ፡ ከኢየሱስ ፡ ሲርቁ
ምን ፡ ያድናቸው ፡ ይሆን ፡ ከጥፋት
የናቁትን ፡ ቸር ፡ መድኅን
ግርማውን ፡ ሲለብስ ፡ ያዩታል ፡ በፍርሃት

ኦ! ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ በቅዱስ ፡ ሕማምህ
ኃጢአተኞችን ፡ አድነሃል
ለመንፈሣችን ፡ ዕረፍት ፡ በድካምህ
እንድጸጠን ፡ ተጨንቀሃል
ሁላችንን ፡ ልታድነን
በቅዱስ ፡ መስቀልህ ፡ ገዝተኸናል

አንተ ፡ በጐልጐታ ፡ ላይ ፡ የሞትህልን
ኦ ፡ ኢየሱስ ፡ ከርስቶስ ፡ ለማመን ፡ እርዳን
የሠራህልንንም ፡ ግለጥልን
እኛም ፡ በመስቀልህ ፡ ኃይል ፡ እንዳን
መስቀልህም ፡ ለዘለዓለም
ተስፋና ፡ ሕይወት ፡ ሊሰጠን ፡ ያብቃን