አዳኜ ፡ ደሙ ፡ ፈሰሰ (Adagne Demu Fesese)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዳኜ ፡ ደሙ ፡ ፈሰሰ
ንጉሤ ፡ ሞተልኝ
ራሱ ፡ ለውርደት ፡ ደረሰ
እኔን ፡ ሊያድነኝ
በመስቀል ፡ በመስቀል ፡ ብርሃን ፡ ባየሁበት
የልቤ ፡ ሸክም ፡ በቀለለበት
በዕምነት ፡ ነው ፡ ማየትን ፡ ያገኘሁ
በዚህ ፡ ደስታዬን ፡ አሳያለሁ

ስላደረግሁት ፡ በደል ፡ ነው
በዛፍ ፡ ላይ ፡ ጭንቀቱ
ርኅሩኅ ፡ ነው ፡ ሰጭ ፡ ፀጋውን
ለዚህ ፡ ነው ፡ መሞቱ
በመስቀል ፡ በመስቀል ፡ ብርሃን ፡ ባየሁበት
የልቤ ፡ ሸክም ፡ በቀለለበት
በዕምነት ፡ ነው ፡ ማየትን ፡ ያገኘሁ
በዚህ ፡ ደስታዬን ፡ አሳያለሁ